በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቱኒዚያው ተንታኝ በሰጡት አስተያየት በቁጥጥር ስር ዋሉ


እ.ኤ.አ. ዛሬ ግንቦት 12 ቀን 2024 የታሰሩ ተቃዋሚዎች እንዲፈቱ የቱኒዚያ እና የፍልስጤም ባንዲራ በማውለብለብ የቱኒዚያ ሰልፈኞች መፈክሮችን አሰምተዋል።
እ.ኤ.አ. ዛሬ ግንቦት 12 ቀን 2024 የታሰሩ ተቃዋሚዎች እንዲፈቱ የቱኒዚያ እና የፍልስጤም ባንዲራ በማውለብለብ የቱኒዚያ ሰልፈኞች መፈክሮችን አሰምተዋል።

የቱኒዚያ የጸጥታ ሃይሎች በቱኒዝ የሚገኘውን የጠበቆች ማህበር በመውረር የህግ ባለሙያ እና የፖለቲካ ተንታኝዋን ሶንያ ዳህማኒን በቁጥጥር ስር አውለዋል፡፡

ዳህማኒ የታሰሩት በቴሌቭዥን ስለ ሀገሪቱ ሁኔታ አስተያየት ከሰጡ በኋላ ነው ሲሉ ጠበቆቿ ተናግረዋል።

ትላንት ቅዳሜ የዳህማኒን መታሰር ሲያሰራጭ የነበረው ፍራንስ 24 የተባለው የቴሌቪዥን ዜና አውታር በዜናው ምክንያት ስርጭቱን ለማቋረጥ መገደዱን አስታውቋል፡፡

ሠራተኞቹ ላይ ጥቃት እንደደረሰባቸው እና ካሜራ ባለሙያዎች ለአጭር ጊዜ እንደታሰሩ ፍራንስ 24 ገልጿል።

የቱኒዚያ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ዳህማኒ “በመገናኛ ብዙሃን “የውሸት ዜናዎችን” እና “የጥላቻ ንግግርን ማነሳሳትን” ይከለክላል በሚል በወጣው አወዛጋቢ አዋጅ 54 መስረት ምርመራ ሲካሄድባቸው ነበር፡፡

አዋጁ ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ከ60 በላይ ጋዜጠኞች፣ ጠበቆች እና ተቃዋሚዎች መከሰሳቸውን የቱኒዚያ ጋዜጠኞች ብሄራዊ ማህበር አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG