በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ጣሊያናዊያን ልጅ እንዲወልዱ ግፊት አደረጉ


የሮማ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ 2016
የሮማ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፤ 2016

የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ ጣልያናውያን ልጆች እንዲወልዱ ለማሳሰብ አርብ ዕለት በነበራቸው ዘመቻ ግፊት አድርገዋል። የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲስ የሀገሪቱ የስነ ሕዝብ አወቃቀር ቀውስ የወደፊቱን አደጋ ላይ እየጣለ መሆኑን በማስጠንቀቅ ጣሊያን ቤተሰቦችን ለመርዳት የረዥም ጊዜ ፖሊሲዎችን እንድታወጣ አሳስበዋል።

ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ከቤተሰብ ደጋፊ ቡድኖች ጋር ባደረጉት ዓመታዊ ስብሰባ “የልደቶች ቁጥር የአንድ ህዝብ ተስፋ የመጀመሪያው አመላካች ናቸው” ያሉ ሲሆን "ህጻናትና ወጣቶች በሌሉበት፤ አገር የወደፊት ፍላጎቷን ታጣለች" ሲሉ ተናግረዋል።

የሊቀጳጳሱ የአሁኑ ጥሪ ብዙ በኢንዱስትሪ የበለጸጉ አገሮችን ፊት ለፊት የተጋፈጡትን የሕዝብ ቁጥር ድርቅ፤ በተለይም ለጣሊያን እና ከዚያ ባሻገር ባሉ የአውሮፓ ሀገራት ላሉት የቀረበ የቅርብ ጊዜ ጥሪ ነው።

የጣሊያን የወሊድ መጠን ከአለም ዝቅተኛዎች መካከል አንዱ ሲሆን ላለፉት ለ15 ዓመታት ያህል እያሽቆለቆለ በመምጣት ባለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት በጣሊያን 379,000 ህጻናት ብቻ በመወለዳቸው ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ይህ የቫቲካን ጠንካራ ድጋፍ የቀኝ ክንፍ መንግስት መሪ የሆኑት የጠቅላይ ሚኒስትሯ ጆርጂያ ሜሎኒ እ.ኤ.አ. በ2033 ቢያንስ በየዓመቱ ግማሽ ሚሊየን ሕፃናት እንዲወለዱ ለማበረታታት የተጀመረውን ዘመቻ የሚደግፍ ነው። ይህ ጥሪ በጣሊያን የአዛውንቶች ቁጥር መጨመር የተነሳ ምጣኔ ሀብቱ እንዳይወድቅ ለመከላከል አስፈላጊ ነው ሲሉ የስነ-ህዝብ ተመራማሪዎች ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG