በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግስታቱ ድርጅት በአፍጋኒስታን በጎርፍ አደጋ 300 ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀ


ባንግላዲሽ፤ 2016
ባንግላዲሽ፤ 2016

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የታሊባን ባለስልጣናት በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ ባግላን ግዛት፤ በጣለው ከባድ የጎርፍ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ቢያንስ 300 መድረሱን፤ ቅዳሜ ዕለት አስታወቁ።

“ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በጣለው ያልተለመደው ከባድ ዝናብ ምክንያት ካደረሳቸው ጉዳቶች ይህ ጎርፍ አንዱ ነው” ያለው የመንግስታቱ ድርጅት የዓለም የምግብ መርሃ ግብር የጎርፍ አደጋው ከ1,000 በላይ መኖርያ ቤቶችን አውድሟል ሲል ገልጿል።

አንድ ከፍተኛ የታሊባን ባለስልጣን በማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ባስተላለፉት የቪዲዮ መልእክት አርብ በደረሰው አደጋ ቢያንስ 150 ሰዎች ባግላን ናህሪን በተባለ አውራጃ መሞታቸውን ተናግረዋል ።

ጉላም ራሶል ቃኒ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ገልፀው በአካባቢው ለማዳን የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ወደ አካባቢው ደረሰዋል ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG