በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን የምድር ጦር የመሳሪያ አቅርቦት ከመቀበሉ በፊት ሩሲያ መግፋቷን እንዳትቀጥል ሰግቷል


ዩክሬናዊያን በናዝሪ ግሬንቪች የቀብር ስነ ስርዓት ላይ፤ 2016
ዩክሬናዊያን በናዝሪ ግሬንቪች የቀብር ስነ ስርዓት ላይ፤ 2016

የዩክሬን የምድር ጦር አዛዥ አርብ ታትሞ በወጣው ቃለ መጠይቃቸው ኪየቭ ባጋጠማት የጦር መሳሪያ አቅርቦት መዘግየት ችግር ምክንያት ሞስኮ በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ልታደርገው በምትችላቸው እንቅስቃሴዎች ለ26 ወራት የዘለቀው ጦርነት ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እንደሚሸጋገር ይጠበቃል ብለዋል።

ጄኔራል ኦሌስካንደር ፓቭሊክ ለዘ ኢኮኖሚስት መጽሔት እንደተናገሩት "በአንድ ወይም በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ በቂ የጦር መሳሪያዎች ካልተቀበልን ሩሲያ ሁኔታው በራሷ ላይ እንደሚብሳባት” ታውቃለች ብለዋል።

በፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን እንዲሰጥ የተጠየቀው የጦር መሳሪያ እርዳታ ጥያቄ በኮንግረስ ውስጥ በተነሳ አለመግባባት በመያዙ አሜሪካ ለዩክሬን የምታደርገው የጦር መሳሪያዎች አቅርቦት ለወራት ቀንሷል። ይህ ውሳኔ የተላለፈው ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ ነበር።

ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አርብ ዕለት እንደተናገሩት ዩክሬን አሁንም ሆነ ወደፊት ቁልፍ የሆኑ የጦር መሳሪያ አቅርቦቶች “በጊዜው” ያስፈልጋታል ብለዋል።

ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት ጄነራል ፓቭሊክ ሞስኮ በምስራቅ ዩክሬን በሉሃንስክ እና በዶኔትስክ ክልሎች የምታደርጋቸውን አዝጋሚ ግስጋሴ ላይ ትኩረቷን አድርጋ ትቀጥላለች ማለታቸውን ዘግቧል። በሌላ በኩል ዩክሬን ተጨማሪ የአየር መከላከያ ትፈልጋለች፣ እናም ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች ሲደርሱ ተጨማሪ ድጋፍ ይሆናታል ብሏል። ጄነራሉ አክለውም “ሩሲያ ከሁሉ የሚመቻትን አማራጭ ከመውሰዷ በፊት በሁሉም መስመሮች ያለንን መረጋጋት ትፈትሻለች” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG