በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ሁለት ተቃዋሚ ራፐሮችን አሰረች


ፎቶ ፋይል - የኢራን ብሔራዊ ባንዲራ የኢራን ኤምባሲ ውስጥ በበርሊን፤ ጀርመን እአአ ታኅሳስ 1/2011
ፎቶ ፋይል - የኢራን ብሔራዊ ባንዲራ የኢራን ኤምባሲ ውስጥ በበርሊን፤ ጀርመን እአአ ታኅሳስ 1/2011

ኢራን ውስጥ 'ተዘጋጅ' የሚል የሙዚቃ ቪዲዮ መውጣቱን ተከትሎ ቫፋዳር በመባል የሚታወቁት የራፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች ዳንኤል ሞጋዳም እና ቫፋ አህመድፑር ታሰሩ፡፡

ትናንት ሐሙስ በቫፋዳር የኢንስታግራም ገፅ ላይ የሰፈረው መልዕክት አህመድፑር እና ሞጋዳም የታሰሩት ሺራዝ ውስጥ ከሰዓት በኋላ 7፡30 መሆኑን ገልጿል፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ያሉበት ትክክለኛ ቦታ እና ሁኔታቸው አልተገለጸም።

ሞጋዳም እና አህመድፑር የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክን በመተቸት የሀገሪቱን ቀውሶች እና የኢራን ህዝብ ያጋጠሙትን ፈተናዎች በጥንታዊቷ ፐርሴፖሊስ ከተማ በተቀረፀው ዜማቸው ላይ አጉልተው አሳይተዋል።

ሞጋዳም በቅርቡ በኢንስታግራም ገጹ ላይ እንዳስታወቀው "ባለሥልጣኖቹ እየወረሩ ነው፤ ህዝቡ ... ቤቱ እየተወረረ ነው ... ቫፋ እና እኔ አንድ ላይ ነን" ሲል ባለሥልጣናቱ እሱን እና ቫፋዳርን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጿል፡፡

ተዋናይ እና ዘፋኙ ሞጋዳም ትላንት ሐሙስ በኢንስታግራም ገፁ ላይ የኢራን መንግስት "ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች እና አርቲስቶች" እንዲፈታ እና "አስገዳጅ የሆኑት የሂጃብ" ህጎች እንዲቆሙ አሳስቧል፡፡ "ኢራንን ከአስጸያፊው የአገዛዝ መዳፍ ነፃ ለማውጣት ተዘጋጅተናል"ም ብሏል።."

አህመድፑር በመድረክ ስሙ ቫፋዳር በሚታወቀው የኢንስታግራም ገፁ ላይ ህዝቡ ለሙዚቃ ቪዲዮአቸው ድጋፍ እንዲያደርግ አሳስቧል ፣ “ይህ ከእስር በፊት የእኔ የመጨረሻ ዘፈን ሊሆን ይችላል… ኢራን ለዘላለም ትኑር” ሲልም ተናግሯል፡፡

ሞጋዳም እና ቫፋዳር ኢስላሚክ ሪፐብሊክን በሚተቹ ጥበባዊ ሥራዎቻቸው ምክንያት ቀደም ሲል ከስለላ ተቋማት ጫናዎች ገጥሟቸው እንደነበር ተገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት ተቃዋሚ ራፐሮች ተይዘው የታሰሩ ሲሆን ሌላኛው ተቃዋሚ ራፐር ቱማጅ ሳሊሂ በኢስፋሃን አብዮታዊ ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ ተፈርዶበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG