በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ የትግራይ ክልል ጉብኝት


በእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ሞሼ ሰሎሞን የሚመራ የእስራኤል መንግሥት ልኡካን ቡድን፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉ ባለሥልጣናት ጋር
በእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ሞሼ ሰሎሞን የሚመራ የእስራኤል መንግሥት ልኡካን ቡድን፣ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የክልሉ ባለሥልጣናት ጋር

በእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ሞሼ ሰሎሞን የሚመራ የእስራኤል መንግሥት ልኡካን ቡድን፣ በትግራይ ክልል የሦስት ቀናት ጉብኝት አድርጓል፡፡

ስድስት አባላትን ያቀፈው የልኡካን ቡድኑ በጉብኝቱ፥ በእርሻ ልማት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና አስቸኳይ ርዳታ ስለሚዳረስበት መንገድ በጋራ መሥራት ስለሚቻልበት ኹኔታ መወያየቱን፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም የእስራኤል ልኡካን ቡድን፣ በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን በዓዲ ዳዕሮ እና እንዳባጉና ከተሞች ነዋሪ ቤተ እስራኤላውያንም ጋራ ተወያይቷል፡፡ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የወደሙ የአካባቢውን መሠረተ ልማቶች መልሶ መገንባት ስለሚቻልበት ኹኔታም ተነጋግረዋል። የአካባቢው ቤተ እስራኤላውያን መካነ መቃብርም በልኡካን ቡድኑ ተጎብኝቷል።

የልኡካን ቡድኑ መሪ የእስራኤል ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ሞሼ ሰሎሞን፣ በጉብኝቱ ፍጻሜ በሰጡት መግለጫ፣ ጦርነቱ በትግራይ ክልል መሠረተ ልማቶች ላይ ያደረሰውን ውድመት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንደሚያስረዱ መናገራቸው ተመልክቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ 10 ሀገራትን በመወከል ማዕከሉን በለንደን ባደረገው “የሮያል ዲፌንስ ኮሌጅ” የሚሠሩ የጸጥታ እና ዲፕሎማሲ ባለሞያዎች፣ ከህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል ጋራ በፕሪቶርያ የሰላም ስምምነት እና በወቅታዊ ኹኔታዎች ላይ ተነጋግረዋል።

ባለሞያዎቹ፣ በተመሳሳይ ጉዳዮች ላይ፣ ከክልሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ጋራ እንደተወያዩ፣ የዓረና ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ዓምዶም ገብረ ሥላሴ ለሪፖርተራችን ሙሉጌታ አጽብሓ ገልጸዋል

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG