በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወጣት ስፖርተኞች ሁለገብ የህይወት ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያግዘው የትሥሥር ተቋም


ወጣት ስፖርተኞች ሁለገብ የህይወት ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያግዘው የትሥሥር ተቋም
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:33 0:00

ወጣት ስፖርተኞች ሁለገብ የህይወት ክህሎት እንዲኖራቸው የሚያግዘው የትሥሥር ተቋም

ከተመሰረተ ሦስት ዓመታትን ያስቆጠረው ስፖርት ፎር ቼንጅ ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ሲሆን ስፖርትን ከሁለገብ እውቀትና ከዕለት ተዕለት ህይወት ጋር እንዲዋሃድ ለማድረግ ግንዛቤ ላይ እየሰራ ይገኛል።ተቋሙ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ከተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር፤ ወጣቶች እና ዐዳጊዎች የስፖርትና የህይወት ክህሎት እና ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግ እንዲሁም በሁሉም የስፖርት ዘርፎች ላይ ያሉ ቡድኖች ከተለያዩ ተቋምት ጋር ትብብሮች እንዲዳብሩ በማድረግ ይሰራል።


በተጨማሪም ተቋሙ የተለያዩ ስፖርት አሰልጣኞች የህይወት ክህሎት እና ሁለንተናዊ ስልጠናዎችን እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል። ኤደን ገረመው የስፖርት ፎር ቼንጅ መስራች እና ዋና ስራ ስፈጻሚ አሃዱ ገብሩን እና በተቋሙ ከሚደግፉ የስፖርት ቡድን አሰልጣኞች መካከል መካከል አንዷን አነጋግራ ያሰናዳቸው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG