በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጥቃት ከመክፈቷ አስቀድሞ ፍልስጤማውያን ራፋን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች


ፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ የእስራኤል ጦር ባዘዘው መሰረት ንብረታቸውን ይዘው እየለቀቁ
ፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ በራፋህ የእስራኤል ጦር ባዘዘው መሰረት ንብረታቸውን ይዘው እየለቀቁ

የእስራኤል የጦር ኃይል በራፋህ ምሥራቃዊ ክፍል የሚገኙ ነዋሪዎች ኻን ዩኒስን የሚጨምር የሰብዓዊ ረድዔት ክልል ሲል ወደገለጸው አካባቢ እንዲያቀኑ ዛሬ ሰኞ አሳስቧል፡፡

እስራኤል ማሳሰቢያውን ያወጣችው ራፋህ ላይ በእግረኛ ጦር ልትከፍት ካቀደችው ጥቃት አስቀድሞ ነው፡፡

የእስራኤል የመከላከያ ኃይሎች ቃል አቀባይ በአረብኛ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ባሰፈረው መልዕክት የእስራኤል ጦር ራፋህ ውስጥ በሚገኙ አሸባሪ ድርጅቶች ላይ የኃይል ርምጃ ስለሚወስድ በዚህ አካባቢ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ህይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል” ብሏል፡፡

እስራኤል በራፋ "ለተገደበ (ወታደራዊ) ዘመቻ" እየተዘጋጀች ነው ያሉት የወታደራዊ ቃል አቀባይ “በግምት ወደ 100,000 የሚሆኑ ሰዎች ቦታውን በተፈቀደው የመውጫ አቅጣጫ ለቀው እንዲወጡ ተጠይቀዋል”.ብለዋል፡፡

እስራኤል “ሃማስን ለማሸነፍ በራፋህ ላይ ጥቃት መሰንዘር አስፈላጊ ነው” ብላለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ሌሎች እስራኤል ከግማሽ በላይ የሚሆነው የጋዛ ህዝብ በተጠለለበት አካባቢ መጠነ ሰፊ ጥቃት ከፈፀመች ሰብዓዊ ጥፋት ሊደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢንጃሚን ኔታኒያሁ ጋር ዛሬ ሰኞ በስልክ መነጋገራቸውን ዋይት ሐውስ አስታውቋል፡፡

ከፍተኛ የሃማስ ባለሥልጣን፣ ነዋሪዎች ራፋን ለቀው እንዲወጡ የተሰጠውን ትዕዛዝ “ ሁኔታውን የሚያባብስ እና መዘዝ የሚያስከትል መዘዝ የሚያስከትል ” ብለውታል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የፍልስጤም የረድኤት ተቋም በማህበራዊ ሚዲያ ዛሬ ሰኞ ባወጣው መልዕክቱ እስራኤል በራፋህ የምታካሂደው ዘመቻ “የተጨማሪ ሲቪሎችን ስቃይ፣ ሞትና ውድመትን ያስከትላል” ብሏል፡፡

በሌላም በኩል መሰረቱን ሊባኖስ ያደረገው የሂዝቦላ ታጣቂ ቡድን ሰሜን እስራኤል የሚገኙ የጦር ሰፈሮችን ኢላማ ያደረጉ በርካታ ሚሳይሎችን መተኮሱን ተናግሯል፡፡ ጥቃቱን የሰነዘረው “እስራኤል በምስራቅ ሊባኖስ ቢያንስ ሶስት ሰዎች ላቆሰለችበት ጥቃት ለመበቀል ነው” ብሏል፡፡

በእስራኤል ና ሀማስ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ለማምጣት ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም ትናንት እሁድ የካታር እና የግብጽ ሸምጋዮች ያደረጉት ውይይት የሀማስ ልኡካን ቡድን ከአመራሩ ጋር ለመምከር ካይሮን በመልቀቃቸው ብዙም ውጤት ያስገኘ አይመስልም፡፡ የልኡካን ቡድኑ ነገ ማክሰኞ ወደ ካይሮ ይመለሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG