በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ድሮኖች በካርኪቭ 6 ሰዎች ላይ ጉዳት አደረሱ


ካርኺቭ ዩክሬን ሚያዚያ 2016
ካርኺቭ ዩክሬን ሚያዚያ 2016

ሩሲያ በዩክሬን ካርኪቭ እና ዲኒፕሮ ክልሎች በአንድ ጀንበር በሰው አልባ አውሮፕላኖች ላይ ባደረሰችው ጥቃት በትንሹ ስድስት ሰዎች ቆስለዋል። በተጨማሪም በጥቃቱ ወሳኝ የሆኑ መሰረተ ልማቶችን፣ የንግድ እና የመኖሪያ ሕንፃዎችን መመታቷን የክልሉ ባለስልጣናት ዛሬ ቅዳሜ አስታውቀዋል።

የሩስያ ጦር በሰሜን ምስራቅ እና በሀገሪቱ መካከል በሚገኙ ክልሎች ላይ ያነጣጠረ 13 የሻሄድ ሰው አልባ ጢያራዎችን ማጥቃቱን የዩክሬን አየር ኃይል አስታውቋል። በተጨማሪም የዩክሬ የአየር መከላከያ ኃይሎች ሁሉንም ሰው አልባ አውሮፕላኖች መጣላቸውንም የአየር ሃይሉ አዛዥ ተናግረዋል።

ነገር ግን የወደቁት ድሮን አካላት በሰሜን ምስራቅ ካርኪቭ ውስጥ በሲቪል ዒላማዎች ላይ በማረፋቸው አራት ሰዎች ሲቆስሉ በቢሮ ህንፃ ላይ የእሳት ቃጠሎ እንደደረሰ የክልሉ ገዥ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ የኢንዱስትሪ ከተማ በሆነችው ዲኒፕሮፔትሮቭስክ ክልል ሁለት ሰዎች ሲቆስሉ ወሳኝ የሆነ የመሠረተ ልማት ግንባታና ሦስት ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል በማለት የክልሉ ገዥ ሰርሂ ሊሳክ ተናግረዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG