በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ‘ለሀማስ ተኩስ ማቆም ቀላል መሆን አለበት’ አሉ


ጋዛ፤ ፍልስጤም
ጋዛ፤ ፍልስጤም

ከእስራኤል ጋር የተኩስ አቁም ስምምነትን መቀበል ለሀማስ “ቀላል ነገር” መሆን ቢገባውም ነገር ግን ታጣቂዎቹ በጋዛ አመራር ዙሪያ ያላቸው ተነሳሽነት ግልፅ አይደለም" ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አርብ ማምሻውን ተናግረዋል።

የጋዛን ሰርጥ የተቆጣጠረው ሃማስ የልዑካን ቡድኑን በድጋሚ ቅዳሜ ዕለት ወደ ካይሮ በመመለስ በግብፅ እና በኳታር አደራዳሪነት ሲካሄድ የቆየውን የእስራኤልን ታጋቾች ለማስፈታት የምታደርገውን ጥቃት በጊዜያዊነት የሚያስቆም ድርድር ለመቀጠል ማቀዱን አስታውቋል።

ብሊንከን “በተግባር የተኩስ አቁም ለማድረግና ታጋቾችን መፍታት ላይ አዎንታዊ መልስ እንደሚሰጡ እንጠብቃለን። ያሉ ሲሆን “በአሁኑ ወቅት ያለው እውነታ በጋዛ ህዝብ እና በተኩስ አቁም መካከል ያለው ሀማስ ብቻ ነው” ሲሉ አክለዋል።

ኔታንያሁ ከብሊንከን ጋር ከመነጋገራቸው በፊት የእርቁ ድርድር ውጤት ምንም ይሁን ምን በደቡብ የጋዛ ከተማ ራፋህ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቃል ገብተዋል።

በአንጻሩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር 1.2 ሚሊዮን የሚገመቱ ፍልስጤማውያን በተጠለሉባት ራፋህ ላይ እስራኤል ላይ ጥቃት እንዳትፈጽም በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋል።

ብሊንከን ዩናይትድ ስቴትስ ለእስራኤል ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ እየሰጠች ቢሆንም ነገር ግን እስራኤል "ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉትን ሲቪሎች በትክክል ለመጠበቅ የሚያስችል አስተማማኝ እቅድ አላቀረበችም" ሲሉ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG