በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በ“ዘንባባው እሑድ” የተገለጸው የኢትዮጵያውያን የሰላም ምኞት

በታላቁ ጾመ ኢየሱስ ሱባኤ ላይ የሚገኙት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን፣ የሱባኤው ስምንተኛ ሰንበት የኾነውን የሆሳዕናን በዓል እሑድ ዕለት አክብረዋል፡፡ የሆሳዕና በዓል በሌላ አጠራር የዘንባባው እሑድ፣ ጌታ ኢየሱስ በአህያ ጀርባ ላይ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ፣ ሕፃናት እና አዕሩግ በዘንባባ ዝንጣፊ እያመሰገኑ የተቀበሉበት ቀን ነው፡፡

የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘጋቢ በተገኘበት የእንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን በዓሉ ሲከበር የተገኙ ምእመናን፣ በአገራቸው ሰላም እንዲሰፍን ምኞታቸውን ገልጸዋል።


XS
SM
MD
LG