በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፍልስጤም አትሌቶች ፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ይጋበዛሉ - ዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ


ፋይል - ግሪክ በተካሄደው ኦሊምፒክ የችቦ ማብራት ስነስርዓት ላይ ችቦውን የለኮሰው የግሪክ አትሌቶ አዮአኒስ ፋውንቶሊስ
ፋይል - ግሪክ በተካሄደው ኦሊምፒክ የችቦ ማብራት ስነስርዓት ላይ ችቦውን የለኮሰው የግሪክ አትሌቶ አዮአኒስ ፋውንቶሊስ

ከስድስት እስከ ስምንት የሚደርሱ ፍልስጤማውያን አትሌቶች በፓሪሱ ኦሊምፒክ ላይ ይወዳደራሉ ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንዶቹ በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ብቁ ሆነው ባይገኙ እንኳን በዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደሚጋበዙ፣ የተቋሙ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባች አስታውቀዋል።

ባች ከአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ጋር አርብ እለት ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፣ እ.አ.አ ሐምሌ 26 ለሚጀምረው የፓሪሱ ኦሊምፒክ ውድድር፣ በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ማጣሪያ ውድድሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ባች የኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋናው መስሪያ ቤት ከሚገኝበት የስዊዘርላንዱ ሎዛን ከተማ በሰጡት ቃለ ምልልስ "ነገር ግን የፍልስጤም አትሌቶች በምንም አይነት ውድድር ማጣሪያዎቹን ማለፍ ባይችሉ፣ የፍልስጤም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንደሌሎች ብቁ አትሌት እንደሌላቸው ብሔራዊ ኮሚቴዎች በሚደረግላቸው ግብዣ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ በግልፅ ቃል ገብተናል" ብለዋል።

ባች አክለው ዓለም አቀፉ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በጋዛ ግጭት ከተቀሰቀሰበት ቀን ጀምሮ፣ "አትሌቶቹ በማጣሪያዎቹ መሳተፍ የሚያስችላቸውን ስልጠና እንዲቀጥሉ የተለያዩ ድጋፎች ሲደረግላቸው ነበር" ሲሉ አስረድተዋል።

ባች የኦሊምፒክ ኮሚቴው፣ በዩክሬን ላይ በተደረገው ወረራ ምክንያት ሩሲያን ያስተናገደበት መንገድ፣ እስራኤል በጋዛ ከሚያካሂደው ጦርነት በተለየ ነው የሚለውን ክስ ውድቅ አድርገዋል።

ሩሲያ ባካሄደችው ወረራ ምክንያት በበርካታ ዓለም አቀፍ ስፖርት ውድድሮች እንዳትሳተፍ ማዕቀብ የተጣለባት ሲሆን አትሌቶቿ እ.አ.አ በ2024 በፓሪስ በሚካሄደው ኦሊምፒክ፣ የሩሲያን ሰንድቅ ዓላማ ወክለው እንዳይወዳደሩ ታግደዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG