በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሐማስ ላቀረበው የተኩስ አቁም ምክረሃሳብ ከእስራኤል ምላሽ አግኝቻለሁ አለ


አንድ የሁቲ ደጋፊ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በየመን ላይ የምታካሂደውን ጥቃት ለመቃወም እና በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያንን ለመደገፍ በተደረገ ሰልፍ ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ሲያውለበልብ
አንድ የሁቲ ደጋፊ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በየመን ላይ የምታካሂደውን ጥቃት ለመቃወም እና በጋዛ ሰርጥ የሚኖሩ ፍልስጤማውያንን ለመደገፍ በተደረገ ሰልፍ ላይ የፍልስጤምን ባንዲራ ሲያውለበልብ

ሐማስ በቅርቡ ላቀረበው የተኩስ አቁም እቅድ፣ ቅዳሜ እለት ከእስራኤል ባለስልጣን ምላሽ ማግኘቱን እና ምላሽ ከመስጠቱ በፊት ግን ዝርዝሩን እንደሚያጠናው፣ የቡድኑ ምክትል የጋዛ ኃላፊ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በኳታር የሚግኙት ካሊል አልሃያ "ሐማስ ለግብፅ እና ለኳታር አሸማጋዮች ላቀረበው ምክረሃሳብ፣ እ.አ.አ ሚያዚያ 13 ከጽዮናዊው ወራሪ ይፋዊ ምላሽ አግኝቷል" ማለታቸው ቡድኑ ባሳተመው መግለጫ ተገልጿል።


ከስድስት ወራት በላይ የቀጠለውን የእስራኤል እና የጋዛ ጦርነት ለማስቆም የሚደረገው ድርድር እስካሁን ስምምነት ላይ መድረስ ያልቻለ ሲሆን፣ ሐማስ ማንኛውም ስምምነት ጦርነቱን ማስቆም አለበት የሚለውን አቋሙን ይዞ እንደቀጠለ ነው።

የግብፅ ልዑካን ቡድን ግጭቱን ለማስቆም እና እ.አ.አ በጥቅምት ሰባት ሐማስ እስራኤልን በወረረበት ወቅት የተወሰዱ ታጋቾችን ለማስመለስ እንደአዲስ ድርድር ማስጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ዙሪያ ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ለመወያየት፣ አርብ እለት ወደ እስራኤል አቅንቷል።

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ባለስልጣን እንዳስረዱት እስራኤል አዲስ ምክረሃሳብ አላቀረበችም። ሆኖም ቀደም ሲል ድርድር ይካሄድበት በነበረው 40 ታጋቾች ፋንታ፣ 33 ታጋቾችን ከሐማስ ማስለቀቅ የሚቻልበትን የተወሰነ የእርቅ ስምምነት ለመቀበል ፈቃደኝነት አሳይተዋል።

ሐሙስ እለት ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች 17 አገራት ቀውሱን ለማስቆም ሐማስ ሁሉንም ታጋቾች እንዲለቅ ጠይቀዋል። ሐማስ በበኩሉ አርብ እለት ባወጣው መግለጫ፣ በማንኛውም ዓለም አቀፍ ጫና እንደማይሸነፍ አመልክቶ "የህዝባችንን ፍላጎትና መብት ላገናዘበ ሀሳብ እና እቅድ ግን ክፍት ነን" ሲል አመልክቷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG