እስራኤል ባለፉት ሳምንታት የሰብዓዊ ረድዔት ተቋማት ጋዛ መግባት እንዲችሉ ለመፍቀድ ትልቅ እርምጃ ወስዳለች ሲሉ የተናገሩት የዩናይትድ ስቴትስ የሰብዓዊ ጉዳዮች ልዩ ልዑክ፣ ሆኖም ጋዛ ላይ የተደቀነው የቸነፈር አደጋ ከባድ በመሆኑ በቀጣይም ብዙ መሥራት እንደሚጠብቅ ዛሬ አሳስበዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ጋዛ ውስጥ ያለውን የከበደ ሰብዓዊ ቀውስ ለማቃለል እስራኤል እርምጃ እንድትወስድ መጠየቃቸው ይታወሳል።
መመዘን የሚችል ተጨባጭ እርምጃ ስራ ላይ የማታውል ከሆነ ዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ አጋሯ ለሆነችው እስራኤል የምትሰጠው እርዳታ ላይ ቅድመ ሁኔታ ሊቀመጥበት እንደሚችልም ፕሬዚደንቱ አሳስበው ነበር።
ዋሽንግተን እስራኤል በወሰደቻቸው እርምጃዎች ረክታ እንደሆነ ለመግለጽ ያልፈለጉት ባለስልጣን፣ እስራኤል ባለፉት ሁለት ተኩል ሳምንታት ትልቅ እርምጃ ወስዳለች ሆኖም አሁንም መቀጠል ይኖርበታል ሲሉ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።
መድረክ / ፎረም