በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኒዤር የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ የሚጠይቅ ሰልፍ ተካሄደ


በኒዤር የአሜርካ ወታደሮች እንዲወጡ ከሚጠይቁ ሰልፎች አንዱ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 13, 2024)
በኒዤር የአሜርካ ወታደሮች እንዲወጡ ከሚጠይቁ ሰልፎች አንዱ (ፎቶ ኤኤፍፒ ሚያዚያ 13, 2024)

በኒዤር የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች እንዲወጡ በመጠየቅ፣ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬ እሁድ ሰልፍ ወጥተዋል።

ወታደሮቿ ሥርዓት በተከተለ መንገድ እንዲወጡ ለማስቻል፣ ዋሽንግተን አንድ ልዑክ ወደ ሃገሪቱ በቅርቡ እንደምትልክ ይጠበቃል። አሜሪካ ወታደሮቿን እንደምታስወጣ ባለፈው ዓርብ አስታውቃ ነበር።

አሜሪካ በኒዤር 100 ሚሊዮን ዶላር ወጪ በማደረግ ለድሮን በረራዎች መነሻና ማረፊያ የገነባች ሲሆን፣ ከአንድ ሺሕ በላይ የሚሆኑ ወታደሮቻም በዚያ እንደሚገኙ ታውቋል።

የድሮን መሠረቱ በሚገኝባት በሰሜን ኒዤር፣ በረሃማ በሆነችው አጋዴዝ ከተማ የተደረገውን ሰልፍ ያስተባበሩት 24 የሚሆኑ የሲቪል ማኅበረሰብ ቡድኖች ሲሆኑ፣ ባለፈው ዓመት በመፈንቅለ መንግስት ሥልጣን ላይ የወጣው ሁንታ ደጋፊዎች እንደሆኑ የኤኤፍፒ ዘገባ አመልክቷል።

ሰልፈኞቹ፣ “ይህ አጋዴዝ ነው፣ ዋሽንግተን አይደለም። የአሜሪካ ወታደሮች ውጡ” የሚል ግዙፍ ባነር ይዘውም ተስተውለዋል።

የፈረንሣይ ወታደሮች ባለፈው ዓመት ኒዤርን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል።

አሜሪካና ፈረንሣይ በምዕራብ አፍሪካ ከሚገኙ የእስልምና አክራሪ ጂሃዲስቶች ጋራ ለሚያደርጉት ፍልሚያ፣ ኒዤር መሠረት ነበረች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG