በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤጊ ወረዳ በቀጠለው ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ


በቤጊ ወረዳ በቀጠለው ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00

በቤጊ ወረዳ በቀጠለው ግጭት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ገለፁ

በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ፣ በመንግሥት ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ቢያንስ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁት ነዋሪዎቹ፣ ሦስቱ አርሶ አደሮች ትላንት ሰኞ ረፋድ ላይ የተገደሉት፣ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላትን ለመፈለግ አሠሣ እያደረጉ በነበሩ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች ነው፤” ብለዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከቤጊ ወረዳ እና ከምዕራብ ወለጋ ዞን እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል የአስተዳደር እና ጸጥታ ቢሮ፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም።

ይኹንና የፌደራሉ መንግሥት፣ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት በሰጣቸው መግለጫዎች፣ ያልታጠቁ ሰዎችን ዒላማ እንደማያደርግ ገልጾ የሚቀርቡበትን ክሶች አስተባብሏል።

ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG