በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል የአየር መከላከያዋ የኢራንን ጥቃት በስኬት መመከቱን አስታወቀች


 ኢራን በእስራኤል ላይ ያስወነጨፈቻቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በኢየሩሳሌም በሰማይ ላይ ታይተዋል።
ኢራን በእስራኤል ላይ ያስወነጨፈቻቸው ሰው አልባ አውሮፕላኖችን እና ሚሳኤሎችን በኢየሩሳሌም በሰማይ ላይ ታይተዋል።


ኢራን ያደረሰችው ጥቃት በመከላከል ረገድ የአየር መከላከያዎቿ ስኬታማ እንደነበሩ እስራኤል ተናገረች ።ቴህራን በበኩሏ እስራኤል አጸፋ ከወሰደች ተጨማሪ ጥቃት እንደምታደርስ አስጠንቅቃለች።

የኢራን ቀንደኛ የጦር ኃይል ፣ እስላማዊ አብዮታዊ ጓድ ባወጣው የቅድመ ንጋት መግለጫ ፣ ከኢራን ግዛት ወደ እስራኤል ሚሳኤሎች እና ድሮኖች(ሰው አልባ አውሮፕላኖች )ን ማስወንጨፉን አስታውቋል ።

የአሁኑ ጥቃት ፣ የኢራን ባለስልጣናት ደማስቆ ውስጥ ከፍተኛ የጦር መሪዎችን እንደገደለ ለተናገሩለት የሚያዚያ 1 ጥቃት አጸፋ እንደሆነ ጓዱ ተናግሯል ። እስራኤል ጥቃቱን ስላመድረሷ ማረጋገጫም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠችም ።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በዛሬው ዕለት እንዳስታወቁት ከየመን እና ከኢራቅ የተነሱትን ጨምሮ ፣ ኢራን ከ300 የሚበልጡ ተወንጫፊዎችን ወደ እስራኤል ተኩሳለች ። ከእነዚህ መካከል 99 በመቶው በእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት ከሀገሪቱ የአየር ድንበር ውጭ መመከታቸውን ተናግረዋል ።


የእስራኤል አየር መንገድ ባለስልጣን በበኩሉ ዛሬ ማለዳ ባወጣው መግለጫ ፣ የእስራኤል አየር ክልል ዳግም ክፍት ሆኗል ። ከቴላቪቭ ቤን ጎሪዮን አየር ማረፊያ የሚደረጉ በረራዎች ሊቀየሩ ይችላሉ ።

ኢራን እስራኤል ለጥቃቶቹ አጸፋ እንዳትሰጥ አስጠንቅቃለች ፣ " (ለአሁኑ) ጉዳዩ እንደተጠናቀቀ ይቆጠራል " ሲል በኤክስ የማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ መልዕክቱን ያሰፈረው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራን ልዑክ " ይሁንና የእስራኤል አገዛዝ ዳግም ስህተት ቢፈጽም ፣ የኢራን ምላሽ በጣም የከበደ ይሆናል " ብሏል ።

ይህ በእንዲህ እያለ የቡድን 7 ሀገራት መሪዎች ኢራን በእስራኤል ላይ ስለደረሰችው ጥቃት ለመወያየት በዛሬው ዕለት የቪዲዮ ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል ።

ዩናይትድ ስቴትስ ፣ጃፓን ፣ ጀርመን ፣ ፈረንሳይ ፣ ብሪታኒያ እና ጣልያንን ያከተተውን ቡድን ለስብሰባ የጠራችው ተረኛዋ ቡድኑ ሰብሳቢ ጣልያን ናት ።

ኢራን በግዛቷ ሆና በእስራኤል ላይ ያደረሰቸው የአየር ጥቃት ፣ በተቃናቃኞቹ የቀጠናው ኃይሎች መካከል ያለው ግጭት መባባሱን አመላካች ሆኗል ። የአሜሪካ ኃይሎች እስራኤልን የሚያግዙ ርምጃዎች እንዲወስዱም ገፋፍቷል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG