በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዝብ በዓላት እና አከባበር ዐዋጅ ማሻሻያ ሕዝባዊነታቸውን እንዳይገድብ ተጠየቀ


የሕዝብ በዓላት እና አከባበር ዐዋጅ ማሻሻያ ሕዝባዊነታቸውን እንዳይገድብ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:51 0:00

የሕዝብ በዓላት እና አከባበር ዐዋጅ ማሻሻያ ሕዝባዊነታቸውን እንዳይገድብ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፥ የሕዝብ በዓላትን፣ የዕረፍት ቀናትንና የበዓላትን አከባበር ለመወሰን በወጣ ዐዋጅ ረቂቅ ላይ ተወያይቶ ለዝርዝር እይታ ለቋሚ ኮሚቴ መርቶታል፡፡

በዐዋጅ ረቂቁ፣ ሕዝባዊ በዓላትን የሚያስተባብሩ የመንግሥት ተቋማት ተሠይመዋል፡፡ የ“ጉዞ ዐድዋ” መሥራች እና የፊልም ባለሞያ ያሬድ ሹመቴ፣ ይህ አሠራር “የበዓላትን ሕዝባዊነት ሊያሳጣ ይችላል፤” ሲል፣ ስጋቱን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

“በዐዋጅ ረቂቁ ዝግጅት ወቅት በቂ ውይይት ሊደረግበት ይገባ ነበር፤” ያሉት የሕግ ባለሞያ አቶ ዳዊት ገብሩ በበኩላቸው፣ አሁንም በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉ ስጋቶችን ለመፍታት፣ ከመጽደቁ በፊት ተገቢው ውይይት እንዲደረግ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG