በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጦርነት በደቀቀው  ዳርፉር የእህል ርዳታ ደረሰ 


ከወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጦርነት በደቀቀው ዳርፉር የእህል ርዳታ ደረሰ
ከወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጦርነት በደቀቀው ዳርፉር የእህል ርዳታ ደረሰ

በሱዳን የቀጠለው ጦርነት በዓለም በእጅጉ የከፋውን የርሃብ ቀውስ ሊያስከትል ይችላል በማለት ሲያስጠነቅቅ የቆየው የዓለም ምግብ መርሐ ግብር ፣ በጦርነት ወደ ወደመው የዳርፉር ግዛት ከወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ በእጅጉ አስፈላጊ የሆነውን ረድኤት ማዳረስ እንደቻለ ትናንት አስታውቋል ።

ተቋሙ በሰሜን ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዳርፉር ለሚገኘው ሩብ ሚሊየን ህዝብ የሚዳረስ ሁለት ምግብ እና ተዛማጅ ድጋፎችን የጫኑ መኪኖች ባለፈው ሳምንት ከቻድ ወደ ዳርፉር መግባታቸውን አስታወቋል ።

የዘገየው ተልዕኮ እንዲቀጥል የተፈቀደው የሱዳን ጦር ሃይሎች በየካቲት ወር በቻድ በኩል ያሉ የሰብአዊ ድጋፍ መተላለፊያዎችን ፍቃድ መሰረዛቸውን ተከትሎ ከተደረገ ረጅም ድርድር በኋላ ነው ብሏል መርሐ ግብሩ ።

“ ከቻድ እስከ ዳርፉር ድንበር ተሻጋሪ ሰብዓዊ ተግባራት ህፃናት በምግብ እጦት እየሞቱባቸው ለሚገኙ ማህበረሰቦች ለመድረስ ወሳኝ ናቸው።” ብለው ሌኒ ኪንዚ የተባሉት በመርሀ-ግብሩ የሱዳን የግኑኝነት ኃላፊ ።

መንገዶቹን ለመክፈት የተካሄደው ረዥም ድርድር ውጤት በማስገኘቱ እፎይታቸውን የገለጹት ኃላፊዋ ፣ የሱዳን ሕዝብ በሁሉም የሰብዓዊ ዕርዳታ መንገዶች በኩል የማያቋርጥ የዕርዳታ ፍሰት እስካላገኘ ድረስ፣ “የሀገሪቱ የረሃብ አደጋ እየባሰ ይሄዳል።” ብለዋል ።

ተቀናቃኞቹ የሱዳን ጦር ሃይሎች እና የፈጣን ደራሽ ኃይሎች ሀገሪቱን ከአንድ አመት በፊት ወደ ጦርነት ከማገዱበት ጊዜ ጀምሮ፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከ8.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ገልጿል ። ከእነዚህ መካከል 6.5 ሚሊዮን የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ናቸው ።
የዓለም ምግብ መርሀ ግብር እንዳለው 18 ሚሊዮን ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ እየተጋለጡ ሲሆን 90 በመቶ የሚሆኑት ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች እንደሚገኙም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG