በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን፣ የሩሲያ ጥቃቶች የኃይል አቅርቦቷን አደጋ ላይ መጣሉን አስታወቀች


ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ በምትገኘው ካሪኪቭ ከተማ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ፣ በአንድ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ተቋም ላይ የእሳት ነበልባል እና ጭስ ይታያል - መጋቢት 22፣ 2024
ሩሲያ ዩክሬን ውስጥ በምትገኘው ካሪኪቭ ከተማ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት ተከትሎ፣ በአንድ የኤሌክትሪክ ማሰራጫ ተቋም ላይ የእሳት ነበልባል እና ጭስ ይታያል - መጋቢት 22፣ 2024

ሩሲያ አርብ እለት ወደ ዩክሬን የተኮሰቻቸው በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሳይሎች እና 60 ሰው አልባ አውሮፕላኖች በሦስት ኃይል ማመንጫዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን እና ከፍተኛ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ማስከተላቸውን የዩክሬን ባለስልጣናት አስታወቁ።

ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንሲኪም፣ ሁለት የውሃ ኃይል ማመንጫዎችን ኢላማ በማድረግ እና፣ በዩክሬን ብቻ ሳይሆን በአጎራባቿ ሞዶቫ የአካባቢ ብክለትን በማድረስ፣ ሩሲያን ከሰዋል።

ጥቃቱ ሩሲያ በመጋቢት ወር የቀጠለችው የተጠናከረ ጥቃት አንድ አካል መሆኑ ተገልጿል።

ባለፈው ሳምንት ሩሲያ ከ190 በላይ ሚሳይሎችን እና 140 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ዩክሬን ላይ ማስወንጨፏን ዘለንስኪ አስታውቀዋል። ጥቃቱ በዩክሬን የኃይል ማመንጫ መሠረተ ልማት ላይ የ11.5 ቢሊየን ዶላር ጉዳት ማድረሱንም፣ የሀገሪቱ የኃይል ሚኒስትር ያስቀመጠው ግምት ያሳያል።

በኃይል ማመንጫዎቹ ላይ የደረሰውን ጉዳት ለመጠገን ወራት ሊወስድ እንደሚችም የዩክሬን ትልቁ የግል ሃይል ድርጅት፣ ዲቴክ ያስታወቀ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ስምንት ጊዜ ጥቃት የደረሰበትን የዲኒፕሮ የውሃ ሃይል ማመንጫ ለመጠገን ደግሞ፣ ዓመታት እንደሚያስፈልግ ባለስልጣናት አመልክተዋል።

በዚህ ምክንያት ዩክሬን የአውሮፓ የምታስገባውን የኃይል መጠን የጨመረች ሲሆን፣ በምላሹ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በሩሲያ የነዳጅ ዘይት ፋብሪካዎች ላይ የምታደርሰውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።

በጥቃቱ ምክንያት፣ የሩሲያ ነዳጅ የማጣራት አቅም ከ10-14 በመቶ በሚገመት ደረጃ መውረዱንም የተለያዩ ግምቶች አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG