በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ የእርዳታ አቅርቦት ወቅት በተፈጠረ ትርምስ አምስት ሰዎች መሞታቸውን የህክምና ባለሙያዎች አስታወቁ


ከቪዲዮ ላይ የተወሰደው ምስል፣ ሊነጋጋ አቅራቢያ ጭለማ ውስጥ፣ ምግብ የጫኑ መኪናዎች በእሳት የተያያዙ ፍርስራሾችን በፍጥነት እያለፉ ሲጓዙ ያሳያል - መጋቢት 30፣ 2024
ከቪዲዮ ላይ የተወሰደው ምስል፣ ሊነጋጋ አቅራቢያ ጭለማ ውስጥ፣ ምግብ የጫኑ መኪናዎች በእሳት የተያያዙ ፍርስራሾችን በፍጥነት እያለፉ ሲጓዙ ያሳያል - መጋቢት 30፣ 2024


ከፍተኛ የረሃብ አደጋ ባንዣበበት የጋዛ ሰርጥ ቅዳሜ እለት በተካሄደ የእርዳታ አቅርቦት ወቅት በተፈጠረ ተኩስ እና መረጋገጥ፣ አምስት ሰዎች መሞታቸውን እና በደርዘን የሚቆጠሩ መቁሰላቸውን የፍልስጤም ቀይ ጨረቃ አስታወቀ።

አዣንስ ፍራንስ የተሰኘው የዜና ማሰራጫ ይፋ ያደረገው ምስል፣ ንጋት አቅራቢያ ላይ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ፣ ሰዎች ሲጮኹና፣ በእርዳታ ማከፋፈያው አቅራቢያ የጭነት መኪናዎች በእሳት የተያያዙ ፍርስራሾችን እያለፉ በፍጥነት ሲጓዙ ያሳያል።

ቀይ ጨረቃ እንደገለጸው ሁኔታው የተከሰተው፣ ወደ 15 የሚጠጉ ዱቄት እና ምግብ የጫኑ መኪናዎች መምጣታቸውን ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከተሰበስቡ በኃላ ሲሆን፣ እርዳታው በሰርጡ ሰሜናዊ ክፍል በሚገኘው ኩዌይት አደባባይ ላይ ሊከፋፈል እቅድ ተይዞ ነበር።

አደባባዩ ቀደም ሲልም የተለያዩ ቀውሶች የተስተናገዱበት ሲሆን፣ እ.አ.አ መጋቢት 23 ቀን በተካሄደ የእርዳታ ማከፋፈል ወቅት የእስራኤል ወታደሮች ተኩስ በመክፈታቸው 21 ሰዎች መሞታቸውን ሐማስ የሚመራው መንግስት አስታውቆ ነበር። እስራኤል ግን ውንጀላውን አስተባብላለች።

ቅዳሜ እለት በደረሰው አለመረጋጋት ከሞቱት አምስት ሰዎች ውስጥ ሦስቱ በተተኮሰ ጥይት መገደላቸውን ቀይ ጨርቃ ጨምሮ ገልጿል።

አንዳንድ የዓይን እማኞች ለአዣንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደተናገሩት፣ የእርዳታ አቅርቦቱን የሚቆጣጠሩት የጋዛ ነዋሪዎች ወደ አየር ሲተኩሱ በአቅራቢያው የነበሩት የእስራኤል ወታደሮች ተኩስ በመክፈታቸው ግርግሩ የተፈጠረ ሲሆን፣ ሁኔታውን በፍጥነት ለማለፍ የሞከሩት የጭነት መኪናዎችም ምግብ ለመውሰድ የተሰበሰቡትን ሰዎች መግጨታቸውን አብራርተዋል።

የዜና ወኪሉ ከእስራኤል ጦር ምላሽ ለማግኘት ሞክሮ አልተሳካለትም።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድጋፍ በዚህ ወር ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከጋዛ ህዝብ ግማሽ የሚሆነው በአሰቃቂ የምግብ እጥረት የሚሰቃይ ሲሆን፣ አስቸኳይ እርዳታ ካልተሰጠ ሁኔታ ወደ አስከፊ ረሃብ እንደሚቀየር አስጠንቅቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG