በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ልዕልት ካትሪን በደረሳቸው የድጋፍ መልዕክት መነካታቸውን አስታወቁ 


ልዕልት ካትሪን በደረሳቸው የድጋፍ መልዕክት መነካታቸውን አስታወቁ
ልዕልት ካትሪን በደረሳቸው የድጋፍ መልዕክት መነካታቸውን አስታወቁ

የዌልስ ልዕልት ካትሪን ፣ የካንሰር የህክምና እያገኙ ስለመሆናቸው ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎ ከመላ ዓለም ዙሪያ በደረሳቸው ድጋፍ ልባቸው በእጅጉ እንደተነካ ተናገሩ።

የ42 ዓመቷ ካትሪን አርብ ዕለት ፣ ካንሰር ዳግም እንዳያንሰራራ የሚገታውን የህክምና ሂደት እየተከታተሉ እንደሆነ በቪዲዮ መልዕክት ለብሪታኒያ ህዝብ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ከዓለም መሪዎች ፣ ቤተሰብ አባላት እና ህዝብ ከፍተኛ የድጋፍ መልዕክት ደርሷቸዋል።

"ለክብርትነታቸው መልዕክት መልስ ይሆን ዘንድ ከእንግሊዝ ፣ ከጋራ ብልጽግና ሀገራት እና ዓለም ዙሪያ በደረሱን የርህራሄ መልዕክቶች ልዑልነታቸው እና ልዕልትነታቸው በእጅጉ ተነክተዋል ። '' ብለዋል ልዕልት ካትሪን እና አልጋ ወራሹ ባለቤታቸው ልዑል ዊልያም ቅዳሜ አመሻሽ ባሰራጩት መግለጫ ላይ።

የቀደመው መልዕክት በልዕልት ካትሪን ጤና ዙሪያ ለሳምንታት ያልህል የቆዩ ግምቶችን ቋጭቷል ። በርካቶች የልዕልቷን ጽናት ሲያደንቁ ሌሎች ደግሞ ልዕልቷ ከህዝብ ዓይን በመሰወራቸው ምክንያት የተነዙ የሴራ ሀተታዎችን ተችተዋል።


ንጉስ ቻርለስ ሶስተኛ ከካንሰር ህመም ጋር ሲታገሉ እንደነበር ባስታወቁ ከሳምንታት በኃላ ፣ የልዕልት ካትሪን ጤና ሁኔታ በግልጽ የማሳወቁ እርምጃ የብሪታኒያን ንጉሳዊ ቤተሰብ ለቀውስ ዳርጎታል።

ከነገሱ 17 ወራትን ያስቆጠሩት ንጉስ ቻርለስ ፣ ለልጃቸው ሚስት ክብር ሲሉ ማናቸውንም ህዝባዊ ተሳትፏቸውን እንደሚሰርዙ አስታውቀዋል ።የ75 ዓመቱ ንጉስ ፣ ልዕልቷ ስለ ጤና ሁኔታቸው ባደረሱት መልዕክት እና ባሳዩት ጽናት ኩራት እንደተሰማቸውም ተናግረዋል።

ዘገባው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ነው ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG