በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተ.መ.ድ ዋና ፀሃፊ የጋዛን ድንበር ሊጎበኙ ነው


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ግብፅ ሲደርሱ፣ የግብፅ ሁለተኛ ጦር መሪ መሐመድ አብደል ራህማን እና የግብፅ ጤና ሚኒስትር ካሌድ አብደል ጃፋር አቀባበል አድርገውላቸዋል - መጋቢት 23፣ 2024
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ግብፅ ሲደርሱ፣ የግብፅ ሁለተኛ ጦር መሪ መሐመድ አብደል ራህማን እና የግብፅ ጤና ሚኒስትር ካሌድ አብደል ጃፋር አቀባበል አድርገውላቸዋል - መጋቢት 23፣ 2024

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ በግብፅ እና በጋዛ ሰርጥ መካከል የሚገኘውን ድንበር ለመጎብኘት ዛሬ ግብፅ ገብተዋል። ዋና ፀሃፊው ጉብኝቱን የሚያካሂዱት፣ እስራኤል ያለ ዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍም ቢሆን፣ ከሐማስ ጋር ለመዋጋት ወታደሮቿን በድንበሩ አቅራቢያ ወደሚገኘው ራፋህ ከተማ እንደምትልክ ባስታወቀችበት ወቅት ነው።

ምንም እንኳን ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ግፊቶች፣ እስራኤል አብዛኛው የጋዛ ህዝብ በተጠለለበት ራፋህ ከተማ ላይ ላይ ልትወስድ ያቀደችውን የምድር ላይ ጥቃት ማስቆም ባይችሉም፣ ጉተሬዥ በጉብኝታቸው ወቅት በድጋሚ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ ያሰማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እስራኤል ያቀደችው ጥቃት ብዙ ሰላማዊ ዜጎችን እንደሚጎዳ እና በጋዛ ሰርጥ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ እንደሚያባብስ ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጥቃቱ ወደፊት እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።

ኔታንያሁ በእስራኤል ጉብኝት ካደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ጋር አርብ እለት በነበራቸው ንግግር "ይህንን በዩናይትድ ስቴትስ ድጋፍ እንደማደርገው ተስፋ አደርጋለሁ፣ ማድረግ ካለብን ግን ብቻችንንም ቢሆን እናደርገዋለን" ብለዋቸዋል።

የጋዛ ጤና ሚኒስትር ከ32 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን መገደላቸውን ያስታወቀ ሲሆን፣ ለስድስት ወር የተካሄደው ውጊያ እንዲቆም የሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረትም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት "አፋጣኝ" የተኩስ ማቆም እንዲደረግ አርብ እለት ያቀረበውን አዲስ እቅድ፣ የአረብ መንግስታት ደካማ ነው ሲሉ ቅሬታ በማሰማታቸው፣ ቻይና እና ሩሲያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብታቸውን ተጠቅመው ውድቅ አድርገውታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG