ህንድ የጭነት መርከብ በመጥለፍ የተጠረጠሩ 35 የሶማሊያ የባህር ላይ ዘራፊዎችን ቅዳሜ እለት ወደ ሞምባይ አምጥታለች። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት፣ የባህር ላይ ኮማንዶዎች የጠለፋ አደጋ የደረሰበትን የጭነት መርከብ መልሰው ከተቆጣጠሩ እና በርካታ ታጋቾችን ካዳኑ በኃላ ነው።
በታህሳስ ወር ጠለፋ የተካሄደበትን መርከብ ህንድ ከአራት ወር በኃላ ያዳነችው ከሶማሊያ የባህር ዳርቻ 480 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ላይ ነው። መርከቧን የማዳኑን ዘመቻ የመራው የህንድ የባህር ኃይል ባወጣው መግለጫ "ዘመቻው የዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎችን በተከተለ እና በቀጠናው የባህር ላይ ጸጥታ እና ደህንነትን ባረጋገጠ መልኩ መከናወኑን" አመልክቷል።
በጠለፋ ወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች ቅዳሜ እለት ለፖሊስ ተላልፈው መሰጠታቸውንም አስታውቋል።
በህንድ ፀረ-የባህር ላይ ውንብድና ሕግ መሰረት፣ ዘራፊዎቹ ሰው በመግደል ወይም የመግደል ሙከራ ጥፋተኛ ሆነው ተገኙ የሞት ፍርድ የሚፈረድባቸው ሲሆን፣ በባህር ላይ ዘረፋ ወንጀል ደግሞ የእድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል።
መድረክ / ፎረም