በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጊዳ አያና ወረዳ አሥር ሲቪሎች ላይ የበቀል ግድያ መፈጸሙ ተገለጸ


 በጊዳ አያና ወረዳ አሥር ሲቪሎች ላይ የበቀል ግድያ መፈጸሙ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:23 0:00

 በጊዳ አያና ወረዳ አሥር ሲቪሎች ላይ የበቀል ግድያ መፈጸሙ ተገለጸ

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ አንዶዴ ዲቾ ቀበሌ፣ በርካታ ሲቪሎች በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እንደተገደሉ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች እና እናት ፓርቲ አስታወቀዋል። ተገደሉ ያላቸውን የአሥር ሰዎች ስም ዝርዝር በመግለጫ ያሰፈረው እናት ፓርቲ፣ በአንድ የመከላከያ ሠራዊት አባል ላይ ባልታወቁ ታጣቂዎች የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ የመንግሥት ኀይሎች በወሰዱት ርምጃ ያልታጠቁ ነዋሪዎች እንደተገደሉ አስረድቷል።

ፓርቲው በስም ከጠቀሳቸው ሟቾች መካከል የሁለቱ እህት እንደሆኑ የተናገሩ አንዲት ወይዘሮ፣ ወንድሞቼ ለክብረ በዓል በሔዱበት የአቦ ቤተ ክርስቲያን አቅራቢያ በመከላከያ ሠራዊት አባላት በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል፤ ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም፡፡

የአገሪቱ ወታደራዊ እና ሲቪል ባለሥልጣናት በቅርቡ በሰጧቸው አስተያየቶች፣ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊትም ኾነ የመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች በአጠቃላይ፣ ሲቪሎችንም ኾነ የሲቪል ተቋማትን ዒላማ አያደርጉም፤ ሲሉ መሰል ውንጀላዎችን ተከላክለዋል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG