በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ አበባ እና አካባቢው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች ታሰሩ


አዲስ አበባ እና አካባቢው በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች ታሰሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:32 0:00

በአዲስ አበባ እና አካባቢው በትጥቅ የታገዘ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ ነበሩ የተባሉ 50 ሰዎች መታሰራቸውን የጸጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ- ኃይል ከፎቷቸው ጋራ በማጋራት አስታውቋል።

ግብረ ኃይሉ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ሃምሳዎቹ ተጠርጣሪዎች፣ በአማራ ክልል ይንቀሳቀሳሉ ካላቸውና “ፀረ ሰላም ኃይል” ሲል ከገለጻቸው አካላት ጋራ የህቡዕ ትስስር አላቸው በማለትም አክሏል። የታሳሪዎቹን ማንነት ለማጣራት ያደረግነው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ ጉዳዩን ከመግለጫው መስማቱን አስታውቋል። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከቤተሰብ አባላት የደረሳቸው መረጃ ኮሚሽኑ ገልጿል። ፡በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት አካል ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG