በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን በከባድ የሙቀት ንዳድ የተነሳ ትምህርት ቤቶችን ዘጋች


ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 18፣ 2024)
ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 18፣ 2024)

በደቡብ ሱዳን የተነሳው ከፍተኛ የሙቀት ንዳድ መንግሥት ለሁለት ሳምንታት ትምህርት ቤቶችን እንዲዘጋ አስገድዶታል።

መንግሥት ውሳኔውን ያሳለፈው በሀገሪቱ ከፍተኛ ሁከት፣የአየር ንብረው ለውጥ ተጽእኖ እና በቅርቡ ከሱዳን ድንበር አሳብረው የመጡ ፍልሰተኞች ቁጥር በጨመረበት ሁኔታው ውስጥ ነው፡፡

የጁባ ነዋሪዎች ሙቀቱን ለመቋቋም ለበረዶ እና ውሃ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ተገደዋል።

ከፍተኛ በሆነው ንዳድ ውስጥ መደበኛ ትምህርትን ማካሄድ የማይቻል መሆኑን ለሮይተርስ የተናገሩት የጁባ ትምሕር ቤት ርዕሰ መምህር አንቶኒ ሞ አላሚን ጨምሮ ለትምህርት ቤቱ መዘጋት የትምህርት ባለሞያዎችን ድጋፍ አግኝቷል፡፡

“ሙቀቱ እጅግ በጣም ከባድ ነው፣ የትምህርት አሰጣጡን በእጅጉ ይጎዳል” የሚሉት አላሚን “ምክንያቱም በዚህ ጊዜ በክፍሉ ውስጥ መቀመጥ አይችሉም፣ ልጆች በክፍሉ ውስጥ በላብ ይጠመቃሉ፣ አስተማሪዎችም እንዲሁ ላብ በላብ ይሆናሉ መማሪያ ክፍሉ ውስጥ ያሉት ልጆች ብዙ ናቸው፣ መጨናነቅ አለ፣ ያ ከሙቀት ጋር ምን ማለት እንደሆነ ታውቃላችሁ" ብለዋል፡፡

ወላጅ እና የአካባቢው የጋሪ ሾፌር የሆኑት ኢማኑኤል ቢዳል ማርቲን ስለ መንግስት ውሳኔ የተደባለቀ ስሜት አላቸው፡፡ ወደ 45 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ ሊደርስ ይችላል ተብሎ ከሚጠበቀው የሙቀት መጠን ልጆቻቸው የተጠበቁ መሆኑን እፎይታ ቢሰጣቸውም ቤት የሚውሉ ልጆቻቸውን የሚጠብቅላቸው ሰው ባለመኖሩ ግን ጭንቀት ያደረባቸውን መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG