በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔፕፋር ለኢትዮጵያ 111 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊሰጥ ነው


በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አርቭን ማሲንጋ እና የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የተገኙበት ውይይት።
በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አርቭን ማሲንጋ እና የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የተገኙበት ውይይት።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት አስቸኳይ ጊዜ የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ዕቅድ /ፔፕፋር/ ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ 2030 ኤች አይቪን ለመቆጣጠር ለምታደርገው ጥረት መርጃ የሚውል 111 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ መፈቀዱን አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የኤድስ ጉዳዮች አስተባባሪ፣ የዓለም አቀፍ የጤና ዋስትና እና የጤና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት አምባሳደር ዶክተር ጆን ኢንኬንጋንሶንግ እርዳታው መፈቀዱን ይፋ አድርገዋል።

አምባሳደር ኢንኬንጋሶንግ የፔፕፋርን ድጋፍ ይፋ ባደረጉበት በኢንተርኔት አማካይነት በተከናወነው ሥነ ስርዓት ላይ በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር አርቭን ማሲንጋ እና የኢትዮጵያ ጤና ሚንስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተገኝተው ንግግር ማድረጋቸውን ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የወጣው መግለጫ አመልክቷል።

የተፈቀደው የገንዘብ ድጋፍ ፔፕፋር እና የኢትዮጵያ ጤና ሚንስቴር ከኤች አይ ቪ ጋራ የሚኖሩ ሰዎችን ፍላጎት ለማሟላት የሚያካሂዱትን መርሐ ግብር ለማስቀጠል እንደሚረዳ ተጠቁሟል። ግጭት ባለባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የጸረ ኤች አይ ቪ አገልግሎቶችን ለማጎልበት እንዲሁም ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎችን ማግኛ መንገዶችን ማጠናከር ላይ ትኩረቱን ያደረገውን እቅድ ለማከናወን እንደሚጠቅም ተመልክቷል። ልጆች፤ ታዳጊዎች እና የጾታዊ ጥቃት ሰለባዎችን የመሳሰሉ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመድረስ ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG