በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋምቢያ ህግ አውጪዎች በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚደረገው ክርክር በኮሚቴ እንዲታይ መሩ


በጋምቢያ ባንጁል የፀረ-ሴት ልጅ ግርዛት ተቃዋሚዎች ከብሔራዊ ምክር ቤት ውጭ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ
በጋምቢያ ባንጁል የፀረ-ሴት ልጅ ግርዛት ተቃዋሚዎች ከብሔራዊ ምክር ቤት ውጭ ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ

እ.አ.አ በ2015 በጋምቢያ ተጥሎ የነበረውን የሴት ልጅ ግርዛት እገዳ ለመሻር የተደረገውን ሙከራ፣ የሀገሪቱ ህግ አውጪዎች በኮሚቴ እንዲታይ ትናንት ሰኞ መርተውታል።

አብዛኛው ህዝቧየእስልምና እምነት ተከታይ በሆነችው ጋምቢያ የሚገኙ የመብት አቀንቃኞች፣ "ህጉ ከፀደቀ፣ የልጃገረዶችን እና ሴቶችን ደህንነት በተሻለ ለመጠበቅ ለዓመታት የተሰራውን ስራ ይቀለብሳል" ሲሉ ፍራቻቸውን ገልፀዋል። እገዳው ከተነሳ፣ "የልጃገረዶችን የወሲብ ስሜት ለመቆጣጠር ያስችላል" በሚል የተሳሳተ አመለካከት በብዛት ከአምስት አመት በታች በሆኑ ልጆች ላይ የሚፈፀመው ግርዛት ለበለጠ ጉዳት እንደሚዳርግም አመልክተዋል።

የሴት ልጅ ግርዛት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው ባህላዊ የማህበረሰብ ባለሙያዎች በሚጠቀሙባቸው እንደ ምላጭ ባሉ መሳሪያዎች ነው።

ግርዛቱ ከባድ የደም መፍሰስ፣ ሞት እና በወሊድ ጊዜ ችግርን ሊያስከትል የሚችል ቢሆንም፣ በተለያዩ የአፍሪካ አካባቢዎች በስፋት የተለመደ ነው።

የሴቶች ግርዛትን ለማስቆም የሚንቀሳቀሰው 'ሴፍ ሀንድስ ፎር ገርልስ' የተሰኘ ሀገር በቀል ተቋም መስራች የሆኑት ጃሃ ዱኩሬ፣ በቀጣይም ሌሎች የሴቶችን መብቶች የሚጠብቁ ህጎች ሊሰረዙ ይችላሉ" የሚል ስጋታቸውን ለአሶሲዬትድ ፕሬስ ገልጸዋል።

በልጅነቷ ግርዛት የተፈፀመባት እና እህቷ በተመሳሳይ ድርጊት ደም ፈስሷት ስትሞት ያየችው ጁኩሬ፣ "ህጉ ከተሻረ፣ ቀጥሎ ያለ እድሜ ጋብቻ እና የቤት ውስጥ ጾታዊ ጥቃትንም ወደሚከላከለው ህግ ይመጣሉ። ይህ የሀይማኖት ጉዳይ አይደለም። ሴቶችን እና ሰውነታቸውን ለመቆጠጠር የሚደረግ ነው" ብላለች።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ እንደሚያሳየው፣ ጋምቢያ ውስጥ ከ15 እስከ 49 ዓመት ከሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ተገርዘዋል።

ከሦስት ሚሊየን ያነሰ ህዝብ ባላት ጋምቢያ የቀረበው አዲሱ ረቂቅ ህግ በሃይማኖት አጥባቂዎች የተደገፈ ሲሆን ዓላማው "ሃይማኖታዊ ንጽሕናን ለመጠበቅ እና ባህላዊ ደንቦች እና እሴቶች እንዳይነኩ ለመከላከል " መሆኑን ይገልጻል።

የሀገሪቱ የእስልምና ሃይማኖት ከፍተኛው ተቋም የሴት ልጅ ግርዛትን "ከእስልምና መልካም ምግባሮች አንዱ" ሲል እንደገለጸው ተጠቅሷል።

ብሔራዊ ኮሚቴ እንዲከራከርበት የተመራው እና የሴት ልጅ ግርዛት ላይ የተጣለው እገዳ እንዲነሳ የሚጠይቀው ረቂቅ ህግ፣ ከሳምንታት በኃላ በድጋሚ ለፓርላማ ቀርቦ ድምፅ ይሰጥበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG