በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ጥቃት ሁለት ሰዎች ሞቱብኝ አለች


ቤልጎሮድ ሩሲያ መጋቢት 2016
ቤልጎሮድ ሩሲያ መጋቢት 2016

የሩሲያ ባለስልጣናት ዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ባለችው ቤልጎሮድ በተሰኘች ከተማ ላይ በፈጸመችው የአየር ድብደባ ሁለት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቁ። የክልሉ ሀገረ ገዥ ቫይቸልሳቭ ግላድኮቭ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ህይወታቸው ሲያልፍ ሌሎች ሦስት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ዛሬ ቅዳሜ የዩክሬን ድሮኖች በፈጸሙት ጥቃት የግዙፉ የሩሲያ የነዳጅ ዘይት ማጣሪያ ዲሚትሪ አዛሮፍ ንብረት በሆነ የነዳጅ ማጣሪያ ላይ ባደረሱት ጥቃት እሳት መነሳቱን ሀገር ገዥው አስታውቀዋል። ሀገረ ገዥው አክለውም በሌላ ነዳጅ ማጣሪያ ላይ በተመሳሳይ ሊደርስ የነበረውን ጥቃት ተከላክለናል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ የዩክሬን ጥቃት የተፈጸመው ሩሲያ በዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ላይ በፈጸመችው ጥቃት 20 ሰዎች መሞታቸውን ተከትሎ ነው። ይህ አርብ ዕለት በሩስያ የተፈጸመው ተቀጣጣይ ሚሳይል ጥቃት በደቡባዊቷ ከተማ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን እነሱምን ለመርዳት በመጡ የአደጋ ጊዜ ባለሞያችም ላይ ሁለተኛ ዙር ሚሳይል ተተኩሷል።

በሩሲያ በአሁን ሰዓት 40 ሰዎች በደረሰባቸው ጉዳት ሆስፒታል ገብተዋል። የዩክሬኑ ፕሬዘዳንት ቮልደሚየር ዘልንስኪ ታዲያ ይሄ ለትላንቱ ጥቃት “ምላሽ ነው” ሲሉ በቪዲዮ ተናግረዋል። በሌላ በኩል ሩሲያዊያን የፕሬዘዳንታዊ ምርጫ ሁለተኛ ቀን ገብተዋል። ፕሬዘዳንት ፑቲን ለቀጣይ ስድስት ዓመታት ለመምራት እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG