በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመጀመሪያዋ እርዳታ ሰጭ መርከብ ጋዛ ደረሰች


ጋዛ ሰርጥ መጋቢት 2016
ጋዛ ሰርጥ መጋቢት 2016

በቆጵሮስ በኩል ክፍት በሆነው በአዲሱ የእርዳታ መስጫ ኮሪደር አማካኝነት የመጀመሪያ ደረጃ እርዳታ ድጋፍ የጫነች መርከብ ትላንት አርብ ጋዛ ደርሳለች። ሀማስ በበኩሉ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥያቄ አቅርቧል።

የአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ የዜና አውታር ምስሎች ማክሰኞች ዕለት ከቆጵሮስ የተነሳቸው የኦፐን አርምስ ተቋም መርከብ በአምስት ወራቱ አስከፊ ጦርነት እርሃብ ላይ ለሆኑት የጋዛ ነዋሪዎች የሚደርስ 200 ቶን ምግብ ጭና መነሳቷ አመላክተዋል። የአለም ማዕከላዊ ማዕድቤት የተሰኘው የዩናይትድስቴትስ ግብረሰናይ ተቋም ኦፐን አርምስ ከተሰኘው ከሌላ ተቋም ጋር በመተባበር ድጋፉን የሚሰጥ ሲሆን የቆርቆሮ ስጋ፣ ዱቄት፣ ሩዝ፣ ተምር፣ እና ጥራጥሬ የመሳሰሉ ምግቦች በድጋሚ ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ተቋሙ ወደ ጋዛ ለመድረስ ተጨማሪ ሰላማዊ የጉዞ መስመሮች እንዲኖሩም ጠይቋል።

የእስራኤል መከላከያ “የአካባቢው ደህነት እንዲጠበቅ” የጸጥታ ሃይሎችን ማሰማራቱን ያስታወቀ ሲሆን መርከቧ በከፍተኛ ምርመራ ማለፏንም ጨምሮ አስታውቋል። በሀማስ ይዞታ ስር የሚገኘው የጋዛ ግዛት የጤና ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ በጋዛ 123 ሰዎች መገደላቸውን እና ሌሎች 36 ሰዎች ደግሞ በማዕከላዊ ኑሴራት በመኖሪያ ቤቶች ላይ በተፈጸመ የአየር ድብደባ መፈናቀላቸውን አስታውቋል።

የዓይን እማኞች በጋዛ ሰርጥ ባለችው ቁልፍ ከተማ ካኻን ዩኒስ እና ሰብዓዊ ቀውሱ እጅግ በከፋባቸው ሰሜናዊ ስፍራዎች የአየር ድብደባ መፈጸሙን አስታውቀዋል። በሌላ በኩል ሙስሊም ምዕመናን የረመዳን ጾም የመጀመሪያ አርብ ጸሎታቸውን ከእየሩሳሌም ጋር ተቀጽላ በሆነው በአል-አቅሳ መስጂድ በከፍተኛ የደህነት ሰዎች እና በተገደበ እንቅስቃሴ ውስጥ ሆነው አሳልፈዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG