በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በሄይቲ ጸጥታ ጉዳይ በሚነጋገረው ጉባኤ ለመካፈል ወደጃማይካ ተጉዘዋል


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከካሪቢያን መሪዎች ጋር በሄይቲ ጉዳይ ለመወያየት ወደ ኪንግሰተን፣ ጃማይካ በሚወስዳቸው አውሮፕላን ሲሳፈሩ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከካሪቢያን መሪዎች ጋር በሄይቲ ጉዳይ ለመወያየት ወደ ኪንግሰተን፣ ጃማይካ በሚወስዳቸው አውሮፕላን ሲሳፈሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንተኒ ብሊንከን ሄይቲ ውስጥ እየተካሄደ ላለው የፖለቲካ ብጥብጥ መፍትሄ ለመፈለግ በሚካሄደው የካሪቢያን ሀገሮች መሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት ዛሬ ወደ ጃማይካ ተጉዘዋል፡፡ ካሪኮም በሚል የምህጻር ስያሜ የሚጠራው የካሪቢያን ሀገሮች ህብረት “ የሄይቲን የጸጥታ ሁኔታ ለማረጋጋት እና ለህዝቧም አስቸኳይ ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ስለሚቻልበት መንገድ ያተኮረ ውይይት እንደሚካሄድ አመልክቷል፡፡

ካሪኮም ለችግሩ መፍትሄ ለመፈለግ የሄይቲ ጠቅላይ ሚንስትር አሪየል ሄንሪን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ወገኖች ሲያነጋግር መቆየቱን አስታውቋል፡፡

ትናንት ዕሁድ የዩናይትድ ስቴትስ የጦር ኃይል የግድ አስፈላጊ ከሆኑት በስተቀር፣ በሄይቲ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ የሚገኙ ሠራተኞቿን ያስወጣች ሲሆን ኤምባሲውን የሚጠብቁ ተጨማሪ የጸጥታ ኃይሎችም መድቧል። ዩናይትድ ስቴትስ የወደችው እርምጃ ብጥብጡ እየተባባሰ መሄዱን እንደሚጠቁም ተመልክቷል።

ሄይቲ ውስጥ የተደራጁ የወሮበሎች ቡድኖች የሚያካሂዱት ብጥብጥ እየተባባሰ የሄደ ሲሆን ብዙ መቶ ሺህ ሰዎች መኖሪያቸው ለቅቀው ተሰድደዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG