በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ አፍሪካና መካከለኛው ምስራቅን ሊጎበኙ ነው


ፎቶ ፋይል፡ የዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሬሎ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ መልዕክተኛ በነበሩበት ወቅት።
ፎቶ ፋይል፡ የዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሬሎ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 ዓ.ም የታላላቅ ኃይቆች አካባቢ መልዕክተኛ በነበሩበት ወቅት።

የዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ልዩ መልዕክተኛ ቶም ፔሬሎ የተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራትን እና መካከለኛውን ምስራቅ ከመጋቢት 2-16 ድረስ እንደሚጎበኙ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቅዳሜ እለት አስታውቋል።

ፔሬሎ ጉዟቸውን አስመልክተው አርብ እለት በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ኤክስ ላይ ባስተላለፉት በቪዲዮ የተቀረፀ መልዕክት፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን እና ዋይት ሃውስን ወክለው እንደሚጓዙ እና፣ የጉዟቸው ዓላማ ጦርነቱን ማስቆም እና ለሱዳን ሕዝብ አስፈላጊውን ሰብዓዊ ርዳታ ለማድረስ መሆኑን ገልፀዋል።

"የሚቀጥሉትን ሁለት ሳምንታት በስደተኞች መጠለያ ካምፖች እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ሱዳናውያንን በማዳመጥ ነው" ያሉት ፔሬሎ፣ ይህንን ጦርነት ለማስቆም እና ለሱዳን ሕዝብ ፍትህ እና ዲሞክራሲ ለማምጣት ከሚረዱ የአፍሪካ አጋሮች ጋራ እንደሚገናኙም ገልፀዋል።

ፔሪየሎ ከሚጎበኟቸው ሀገሮች ውስጥ ዩጋንዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ግብፅ፣ ሳዑዲ አረብያ እና የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ይገኙበታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG