በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሞ ሳላህ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች አይሳተፍም


ሳዲዮ ማኔ እና ሞ ሳላህ (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)
ሳዲዮ ማኔ እና ሞ ሳላህ (ፎቶ ፋይል፣ ኤፒ)

የግብፅ ብሔራው ቡድን እና የሊቨርፑል ኮከብ አጥቂው ሞ ሳላህ አገሪቱ ላለባት ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች እንደማይሳተፍ አሰልጣኙ ሆሳም ሃሳን ዛሬ እሁድ አስታውቀዋል።

በተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ለሚደረጉ ጨዋታዎች እንዲሁም ግብፅ ከክሮዬሽያ፣ ቱኒዚያ እና ኒው ዚላንድ ጋራ ላለባት የወዳጅነት ጨዋታ ሞ ሳላህ እንደማይሳተፍ ታውቋል።

ውሳኔው የመጣው የሊቨርፑል ቡድን ሞ ሳላህ የሕክምና ዕረፍት እንዲያገኝ መጠየቁን ተከትሎ ነው። ሞ ሳላህ ባለፈው ወር በተደረገው የአፍሪካ ዋንጫ ውድድር ቋንጃው ላይ ጉዳት ደርሶበት ነበር።

ሞ ሳላህ በቅርቡ ለሊቨርፑል የተጫወተው ለ 46 ደቂቃዎች ብቻ ነው። ከብሬንትፈርድ ጋራ ባለፈው ወር በነበረው ጨዋታ ተቀይሮ በመግባት እንዲሁም ባለፈው ሐሙስ በአውሮፓ ሊግ ጨዋታ ከስፓርታ ፕራግ ጋር በነበረው ጨዋታ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG