በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእርዳታ መርከብ ከቆጵሮስ ወደ ጋዛ ሊጓዝ መሆኑን የአሜሪካ እርዳታ ድርጅት አስታወቀ


ኦፕር አርም የተሰኘው የእርዳታ ቡድን ንብረት የሆነው መርከብ፣ ወደ ጋዛ የሚጓዝ 200 ቶን የሚጠጋ ሩዝ እና ዱቄት ቆጵሮስ ላይ ሲጭን - መጋቢት 8፣ 2024
ኦፕር አርም የተሰኘው የእርዳታ ቡድን ንብረት የሆነው መርከብ፣ ወደ ጋዛ የሚጓዝ 200 ቶን የሚጠጋ ሩዝ እና ዱቄት ቆጵሮስ ላይ ሲጭን - መጋቢት 8፣ 2024

ወደ ጋዛ የሚጓዝ እርዳታ ቆጵሮስ ላይ በሚገኝ መርከብ እየተጫነ መሆኑን አንድ የአሜሪካ በጎ አድራጎት ድርጅት አስታወቀ። ጭነቱ በጦርነት ወደሚታመሰው አካባቢ በባህር ላይ የሚጓዝ የመጀመረው መርከብ ሲሆን፣ የአውሮፓ ህብረት መተላለፊያ ኮሪደሩ በዚህ ሳምንት እንደሚከፈት ተስፋ ያደርጋል።

'ኦፕን አርምስ' የተሰኘው እና፣ የስፔንን ባንዲራ የሚያውለበልበው መርከብ፣ ለጋዛ ሰርጥ በጣም ቅርብ በሆነችው የአውሮፓ ሀገር ቆጵሮስ በሚገኘው ላርናካ ወደብ ላይ የቆመው ከሶስት ሳምንት በፊት ነው።

የእርዳታ ቡድኑ አርብ እለት ባወጣው መግለጫ "ቆጵሮስ የሚገኘው ወርልድ ሴንተራል ኪችን የተሰኘ ቡድን፣ በርካታ የሰብዓዊ እርዳታ እቃዎችን ወደ ሰሜናዊ ጋዛ ወደሚጓዘው መርከብ ላይ እየጫኑ ነው ብሏል። "

ላርናካ የሚገኙት የአውሮፓ ኮሚሽን ኃላፊ ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን፣ ቀደም ሲል የባህር መተላለፊያ ኮሪዶሩ እሁድ ይከፈታል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ተናግረው የነበረ ቢሆን ዝርዝር ጉዳዮችን ግን ግልፅ አላደረጉም።

በአሁኑ ወቅት ጋዛ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ወደቦች የሌሉ ሲሆን፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሰርጡ የሚጓዘው ጭነት የት እንደሚራገፍ፣ በእስራኤል ፍተሻ ይደረግባቸው እንደሆነ እና ማን እንደሚያከፋፍላቸው እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የሆነው ፔንታገን አርብ እለት ባወጣው መግለጫ ግን፣ አሜሪካ ጋዛ ውስጥ ለማቋቋም ያሰበችው "ጊዜያዊ የባህር ወደብ" እስከ 60 ቀናት ሊፈጅ እንደሚችል እና 1 ሺህ የአሜሪካ ሰራተኞችም እንደሚሰማሩ አስታውቆ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG