በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የኖቤል ተሸላሚ መሐመድ ዩኑስ በዋስትና ተለቀቁ 


በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የኖቤል ተሸላሚ በዋስትና ተለቀቁ
በሙስና ወንጀል የተከሰሱት የኖቤል ተሸላሚ በዋስትና ተለቀቁ

የባንግላዲሽ ፍ/ቤት በማጭበርበር ወንጀል ለተከሰሱት የኖቤል ሽልማት አሸናፊ ሞሃመድ ዩኑስ የ2.3 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ዋስትና ፈቀዶላቸዋል ።

በ2006 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ለድህነት የተዳረጉ ህዝቦችን ለመርዳት የአነስተኛ ብድር አገልግሎትን በፈርቀዳጅነት በማስጀመራቸው የኖቤል ሰላም ሽልማትን ያሸነፉት ዩኑስ ፣ የሀገሪቱን የስራ ህግ ጥሰዋል በሚል ሌላ ክስ በጥር ወር የ6 ወር እስራት ተፈርዶባቸው ነበር። ከክሱ ጋር በተያያዘ ይግባኝ የጠየቁት ዩኑስ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸዋል ።

የሀገሪቱ ዐቃቢ ህግ ሚር አህመድ አሊ ሳላም ፣ የአሁኑ ማጭበርበር(ሙስና) ክስ ከሀገሪቱ ግዙፍ የተንቀሳቃስ ስልኮች ኩባንያ 34.2% የሚይዘውን ጋርመን ቴሌኮም ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ፈንድ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አስታውቀዋል ።

"ክሱ ከ250 ሚሊየን በላይ ታካ (የሀገሪቱ ገንዘብ) ዝርፊያ እና ህገወጥ የገንዘብ ዝውውርን ያካትታል።ተከሳሹ ፣ ገንዘቡን ከሰራተኞች ይልቅ ለንግድ ማኅበራት መሪዎች ሰጥተዋል።በዚህም መደበኛ ሰራተኞች ተገቢውን ገቢ እንዳያገኙ አድርገዋል።" ብለዋል ዐቃቢ ህግ ሳላም ።

ዩኑስ እና ሌሎች ሰባት ተከሳሾች እሁድ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ሌሎች 6 ሰዎች አልተገኙም።

ዩኑስ ጠበቃ አብደላ አል ማሙን የ83 ዓመቱ ደንበኛቸው እና ሌሎች ተከሳሾች ጥፋት የለባቸውም ብለዋል ።

ባለፈው ዐመት ከ170 በላይ የዓለም መሪዎች እና የኖቤል ተሸላሚዎች የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክ ሐሲና በዩኑስ ላይ የተጀመሩ የህግ ሂደቶችን እንዲያስቆሙ አሳስበዋል።

የኑስ ከሐሳና ጋር ባላቸው የሻከረ ግንኙነት ምክንያት ለጥቃት ተደርገዋል ይላሉ ደጋፊዎቻቸው ። የሀገሪቱ መንግስት ግን የሚቀርቡበትን ውንጀላዎች አይቀበልም ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG