በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራናዊው ተሸላሚ ድምጻዊ ከሶስት ዓመት በላይ ተፈረደበት


ሸርቪን ሐጂፑር -
ሸርቪን ሐጂፑር -

ባላፈው ዓመት በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ቀዳማይ እመቤት ጂል ባይደን የተበረከተለትን የግራሚ ሽልማት ያሸነፈው ኢራናዊ ዘፋኝ ሸርቪን ሐጂፑር ኢራን ውስጥ ከሶስት ዓመት የሚበልጥ እስራት ተፈረደበት፡፡

ሐጂፑር የተሸለመው እኤአ በ2022 የተገደለችውን ማሻ አሚኒን በመደገፍ ባወጣው ሀገራዊ ዜማ ነው፡፡

ሐጂ ዜማውን ኢራን የብሄራዊ ምክር ቤት ምርጫ በምታካሂድበት ተመሳሳይ ቀን በኢንስታግራም የማህበራዊ መድረክ ላይ ማውጣቱ ለተፈረደበት እስራት ተጨማሪ ምክንያት ሆኖበታል፡፡

ሶስት ዓመት ከስምንት ወራት የተፈረደበት ሐጂፑር የተከሰሰው “ሥርዐቱን በመቃወም ፕሮፖጋንዳ በመንዛት” እና “ሰዎችን ለተቃውሞ በማነሳሳት” ነው፡፡

ዜማውን አስመልክቶ “ምንም ጸጸት አላሳየም” ያለው ፍርድቤቱ ለእስሩ ማጠናከሪያ አድርጎ ወስዶታል፡፡

ፍርድ ቤቱ በድምጻዊው ላይ የሁለት ዓመት የጉዞ እገዳ የወሰነበት ሲሆን “የዩናይትድ ስቴትስን ወንጀሎች” አስመልክቶ ዘፈን እንዲያወጣና እነዚያን ወንጀሎችንም በኢንተርኔት እንዲያወጣቸው አዞታል፡፡

ሙሉ ትኩረታቸውን ዓርብ በተካሄደው ምርጫ ላይ ያደረጉት የኢራን መንግሥት መገናኛ ብዙሃን ለሐጂፓወር ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፡፡

ጠበቆቼ እና የኔ ወኪል ላደረጉልኝ ድጋፍ አመሰግናለሁ፡፡” ያለው ሐጂፑር “ የዳኞቹንና የጠበቆችን ስም ግን አልጠቅስም ምክንያቱም ባለመጥቀሴ አይሰደቡም፣ ማስፍራሪያ ዛቻ አይደርስባቸውም፡፡ ማስፈራራያና ዛቻዎች የሰብዊነት ሀይማኖት አይደሉምና” ብሏል፡፡

ለተወሰነ ጊዜ ታስሮ በዋስ የተፈታው ሐጂፑር ውሳኔውን ተከትሎ ወደ እስር ቤት ስለመላክ አለመላኩ አልታወቀም፡፡

በኒዮርክ የተባበሩት መንግስታት የኢራን ልዑክ ስለጉዳዩ ምላሽ አልሰጡም፡፡

“ባራዪ” የተሰኘው ዜማው “በጎዳናዎች ላይ ለደነስነው፣ ስንስም ለሚሰማን ፍርሃት” የመሳሰሉት አገላለጾች ያሉት የሐጂፑር ዜማ፣ በብዙ ኢራናውያን ዘንድ እንደ ሀገራዊ መዝሙር ተወስዷል፡፡

ዜማውን በርካታ ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ የተቀባበሉት ሲሆን የአሚኒኒን ሞት ተከትሎ ኢራን ውስጥ ለተቀሰቀሰው ትልቅ ተቃውሞ ተጨማሪ ድጋፍ ሰጥቷል፡፡

እኤአ በመስከረም 2022 ሂጃብ በአግባቡ አልተከናነብሽም በሚል በስነምግባር ፖሊሶች የተገደለችውን የ22 ዓመቷን የማሻ አሚኒን ሞት ተክትሎ የተነሳው ተቃውሞ የኢራን መንግሥት እንዲወገድ እስከ መጠየቅ የደረሰ ሲሆን በተነሳው ሁከትም 500 ሰዎች ሲሞቱ ከ22000 በላይ ሰዎች ታስረዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG