በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሁቲዎች ተመታ የነበረችው መርከብ ሰጠመች


ሩቢማር የጭነት መርከብ ከየመን ባህር ዳርቻ ስትስጥም እኤአ የካቲት 27 2024 የተወሰደ ምስል
ሩቢማር የጭነት መርከብ ከየመን ባህር ዳርቻ ስትስጥም እኤአ የካቲት 27 2024 የተወሰደ ምስል

ቀይ ባህር ላይ በየመን ሁቲዎች የተመታ አንድ መርከብ ለቀናት ውሃ ላይ ከቆየ በኋላ መስጠሟን ባለሥልጣናት ዛሬ ቅዳሜ አስታወቁ፡፡

እስራኤል በሐማስ ላይ በጋዛ ሰርጥ ከምታካሄደው ጦርነት ወዲህ የወደመች የመጀመሪያዋ መርከብ መሆኗን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ሩቢማር የተባለችው የጭነት መርከብ የሰጠመችው ሁቲዎቹ ከእስያ ወደ መካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ በሚወስደው የጭነትና የኃይል ማመላለሻ በሆነው ወሳኝ የውሃ መስመር ላይ የሚመላለሱ መርከቦችን ማጥቃት በጀመሩበት ወቅት ነው፡፡

እኤአ የካቲት 18 በሁቲዎቹ ጸረ መርከብ ሚሳዬል ፣ የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሠላጤን በሚያገናኘው በባብ ኤልማንዴብ ሰርጥ፣ የተመታችው መርከብ፣ ለቀናት ወደ ሰሜን አቅጣጫ ለመጓዝ እየቀዘፈች ስትቃትት እንደነበር ተገልጿል፡፡

በርካታ መርከቦች ከዚህ መስመር ራሳቸውን እያራቁ ሲሆን የዚህች መርከብ መስጠም መርከቦች ከአካባቢው የበለጠ እንዲርቁ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል፡፡

ይህም ለመርከቦቹ የሚሰጠው የዋስትና መድህን ዋጋ እንዲጨምር ሲያደርግ የዓለምን የዋጋ ግሽበት እንደሚያንር በአካባቢው የሚተላለፉ የርዳታ ጭነቶችንም ሊጎዳ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

በማከላዊ ምስራቅ አሜሪካ የምትገኘውና ቤኒዝ የተባለችውን ሀገር አርማ ያነገበችው ሩቢማር፣ መሠረቱን ሊባኖስ ባደረገ ድርጅት የምትተዳደር ንብረትነቷ እንግሊዝ አገር የሚገኝ አንድ የጭነት መርከብ ኩባንያ መሆኗ ተገልጿል፡፡

በዩናይትድ ስቴትትስ የተመሩ በርካታ የአየር ድብደባዎች የተካሄዱባቸው ቢሆንም፣ ሁቲዎቹ አሁንም ጉዳት የማድረስ አቅማቸው እንዳለ መሆኑ ታውቋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG