በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋዛ ምግብ በመቀበል ላይ የነበሩ ከ100 በላይ ፍልስጤማውያን ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ


በጥቃቱ የተገደለ የፍልስጢየም ነዋሪን አስከሬን በጋዛ ከተማ ወደሚገኙ የእርዳታ መኪናዎች ሲጣደፉ፤ ጋዛ ከተማ፣ እአአ የካቲት 29/2024
በጥቃቱ የተገደለ የፍልስጢየም ነዋሪን አስከሬን በጋዛ ከተማ ወደሚገኙ የእርዳታ መኪናዎች ሲጣደፉ፤ ጋዛ ከተማ፣ እአአ የካቲት 29/2024

እስራኤል ትላንት ሐሙስ በጋዛ ፈጽመዋለች በተባለ ጥቃት 112 ፍልስጤማውያን መገደላቸውን እና ቁጥራቸው የበዛ ሰዎች መቁሰላቸውን የዐይን እማኞችና የጋዛ የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ሰብአዊ ርዳታን ለመቀበል በተሰባሰቡ ፍልስጤማውያን ላይ ነው መባሉ ዓለም አቀፍ ውግዘት አስከትሏል።

እስራኤል ፈጽመዋለች የተባለውን ጥቃት ያስተባበለች ሲሆን ሰዎቹ የሞቱት በተፈጠረው መተረማመስ በደረሰው የርስ በርስ መረጋገጥ እና ከትርምሱ ለማምለጥ ሲሸሹ በነበረው የርዳታ መኪኖች ተገጭተው ነው ብላለች፡፡

የጋዛ ሆስፒታል ባለሥልጣናት መጀመሪያ ላይ በሰጡት መግለጫ የእስራኤል ጥቃት የደረሰው በጋዛ ከተማ ምዕራባዊ ክፍል አል ናቡሲ የትራፊክ አደባባይ ላይ በተሰባሰቡ ፍልስጤማውያን ላይ ነው ብለዋል።

የዐይን እማኞች ደግሞ ወደ ኋላው ላይ እንደተናገሩት ርዳታ ከተጫነባቸው መኪኖች ላይ ዱቄት እና የታሸጉ ምግቦችን ጎትተው ለመውስድ በተሰባሰቡ ሰዎች ላይ የእስራኤል ወታደሮች ተኩስ መከፍታቸውን ተናግረዋል፡፡

የእስራኤል ባለሥልጣናትም መጀመሪያ ላይ በሰጡት መግለጫ ወታደሮቹ ተኩሱን የከፈተቱት ርዳታ ወደ ጫኑት ተሽከካሪዎች የተንጋጉ ሰዎች “አስጊ” ናቸው ብለው ስላሰቡ መሆኑን ተናግረው ነበር፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ X በተባለው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ትናንት ሐሙስ ረፋዱ ላይ ባወጡት የቪዲዮ መግለጫ ግን ወታደሮቹ ህዝቡን ለመበተን “ጥቂት የማስጠንቀቂያ ጥይቶችን ተኩሰዋል” ብለዋል።

በርዳታ ተሽከርካሪዎች በጫኑት ተሽከርካሪዎችም ላይ የተቃጣ ምንም ዓይነት ጥቃት አለመኖሩን ጨምረው የገለጹት ቃል አቀባዩ የእስራኤል ታንኮች 38 የሚደርሱት የርዳታ ተሽከካሪዎች በሰላም የሚያልፉበትን የሰብአዊ እርዳታ መተላለፊያ መስመር ደህንነት ሲጠብቁ ነበር ብለዋል።

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ጋዛ የደረሰው የርዳታ እህል እጅግ አነስተኛ በመሆኑ ረሀብ ጠንቷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ከፍተኛ ረሀብ አደጋ እንደሚከሰት አስጠንቅቋል።

ዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ኦሊቪያ ዴልተን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት "በቅርቡ የተፈጸመው ክስተት መጣራት ይኖርበታል" ያሉ ሲሆን በሰሜን ጋዛ የተፈጸመውን ድርጊት “በጣም አስደንጋጭና በእጅጉ የሚያሳስበን ነው” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG