በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ ደሴ የየብስ ትራንስፖርት ከተቋረጠ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል


የአዲስ አበባ ደሴ የየብስ ትራንስፖርት ከተቋረጠ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:08 0:00

የአዲስ አበባ ደሴ የየብስ ትራንስፖርት ከተቋረጠ ሦስተኛ ቀኑን ይዟል

መንግሥት፣ ጽንፈኛ ሲል በጠራቸው ኀይሎች ላይ እወስዳለኹ ባለው ርምጃ ሰላማዊ ዜጎችን ከጉዳት ለመታደግ በሚል፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ከተቋረጠ፣ ዛሬ ሰኞ ሦስተኛ ቀኑን እንደያዘ፣ ቪኦኤ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ገለፁ።

የየብስ ትራንስፖርት እገዳው፣ ባለፈው ሳምንት በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ሰንበቴ አካባቢዎች በስፋት ሲከሠት የነበረውን ተሽከርካሪዎችን አስቁሞ ተሳፋሪዎችን የማገትና የመግደል እንቅስቃሴ ጋብ ማድረጉን ነዋሪዎቹ ጨምረው ገልፀዋል።

ምንጮቹ እንደገለጹት፣ የየብስ ትራንስፖርት እገዳው፣ ባለፈው ሳምንት በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ሰንበቴ አካባቢዎች በስፋት ሲከሠት የነበረውን ተሽከርካሪዎችን አስቁሞ

ተሳፋሪዎችን የማገትና የመግደል እንቅስቃሴ ጋብ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን፣ መሠረታዊ ሸቀጦችን ማስገባት ባለመቻሉ የዋጋ መናር እየተከሠተ እንደኾነ አመልክተዋል፡፡

ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞንም ሆነ ከሰሜን ሸዋ መንግሥታዊ አመራሮች መረጃ ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም፡፡

ይኹንና፣ በደብረ ብርሃን መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በወጣው የሰሜን ሸዋ ኮማንድ ፖስት ውሳኔ እንደተገለጸው፣ ከየካቲት 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ከደሴ ወደ ሸዋ ሮቢት እና ደብረ ብርሃን እንዲሁም ከደብረ ብርሃን ወደ ሸዋ ሮቢት እና ደሴ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም ተደርጓል፡፡

የእንቅስቃሴው እገዳ፣ በአካባቢው በሚንቀሳቀሱና መንግሥት ጽንፈኛ ሲል በጠራቸው ኀይሎች ላይ ርምጃ እየወሰደ በመኾኑ ሰላማዊ ዜጎችን ከጉዳት ለመታደግ እንደኾነ ውሳኔው አስረድቷል፡፡ የተባለው ርምጃ በምን ያህል ቀናት እንደሚጠናቀቅና የየብስ ትራንፖርት አገልግሎቱ እንደሚጀመር ግን ያለው ነገር የለም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG