በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ የአህጉራዊው የብስክሌት ውድድር አሸናፊ ሆነች


በአፍሪካ አህጉር ትልቅ ስም ካላቸው የብስክሌት ስፖርት መድረኮች አንዱ በሆነው "ቱር  ደ ርዋንዳ 2024"   ውድድር ኤርትራ በቡድን   አንደኛ በመውጣት  አጠናቃለች ።
በአፍሪካ አህጉር ትልቅ ስም ካላቸው የብስክሌት ስፖርት መድረኮች አንዱ በሆነው "ቱር  ደ ርዋንዳ 2024"   ውድድር ኤርትራ በቡድን   አንደኛ በመውጣት  አጠናቃለች ።

በአፍሪካ አህጉር ትልቅ ስም ካላቸው የብስክሌት ስፖርት መድረኮች አንዱ በሆነው "ቱር ደ ርዋንዳ 2024" ውድድር ኤርትራ በቡድን አንደኛ በመውጣት አጠናቃለች ። ትናንት ፍጻሜውን ባገኘው 90 ኪ.ሜ የሚያካልለው 8ኛው የውድድር ምዕራፍ ላይ ፣ የእስራኤል ብሄራዊ ቡድንን የወከለው እንግሊዛዊው ፕሪመር ቴክ ጆሰፍ ብላክሞን የቀዳሚነት ደረጃን በመያዝ አሸንፏል።

ኤርትራዊው ዳዊት የማነ በበኩሉ "የአፍሪካ ምርጥ ብስክሌተኛ!" የሚል ክብር የተጎናጸፈ ሲሆን ፣ የ19 ዓመቱ ሌላው ኤርትራዊ ኣኽሊሉ ኣረፋይነ ደግሞ "ምርጥ አፍሪካዊ ወጣት ተወዳዳሪ" በሚል ሽልማት ተቀብሏል።

ቱር ደ ሩዋንዳ በአውሮፓዊያኑ 1988 በመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ በምትገኘው ርዋንዳ የተጀመረ ውድድር ሲሆን ፣ ከ2009 የአውሮፓ አቆጣጠር ጀምሮ ከዓለም አቀፉ የብስክሌት ፌዴሬሽን የብቃት መመዘኛ ማሟላቱ ተረጋግጦለት ትልቅ ስም ካላቸው ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተመድቧል።

ኤርትራ ከዘንድሮው የቡድን እና የተናጠል የስፖርቱ ዘርፍ ድሎቿ በተጨማሪ ከዚህ ቀደም በተደረጉ ውድድሮች የአሸናፊነት ማዕረግን ደጋግማለች ። መርሃዊ ቅዱስ በ 2019፣ ናትናኤል ተስፋጽየን በ2020፣ ሄኖክ ምሉእ ብርሃን ደግሞ በ2023 የአውሮፓዊያኑ ዘመን የአህጉራዊው ውድድር ባለ ድል በመሆን በውድድሩ ባለታሪኮች መዝገብ ላይ የግል እና የሀገራቸው ስም እንዲሰፍር አድርገዋል ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG