በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በኒው ዮርክ ፍርድ ቤት ለተወሰነባቸው የ454 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ይግባኝ ጠየቁ


ፎቶ ፋይል፡ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ኒው ዮርክ ፍርድ ቤት እአአ ጥር 11/2024
ፎቶ ፋይል፡ የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ኒው ዮርክ ፍርድ ቤት እአአ ጥር 11/2024

የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ የኒው ዮርክ ፍርድ ቤት እንዲከፍሉ የወሰነባቸውን የ454 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት በመቃወም ዛሬ ሰኞ ይግባኝ ጠየቁ፡፡

ትረምፕ የይግባኝ አቤቱታ ለታዋቂነትና ፕሬዝዳንትነት ያበቃቸውን ግዙፍ የህንጻዎች ንብረት እና ገጽታቸውን በገነቡባቸው ዓመታት ዋሽተዋል በሚል ፍርድ ቤቱ የወሰነባቸውን የቅጣት ውሳኔ ነው፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ጠበቆች እኤአ የካቲት ቀን 16 ዳኛ አርተር ኢንጎሮን የክፍለ ግዛቷ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሌቲሺያ ጄምስ ባቀረቡት ክስ ላይ የሰጡትን ብይን እንዲሽር የጠየቁበትን ይግባኝ ማመልከቻ ለኒዮርክ ክፍለ ግዛት መካለኛ ደረጃ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት አስገብተዋል፡፡

የትረምፕ ጠበቆች ለፍርድ ቤቱ ባቀረቡት ማመልከቻ ላይ ዳኛው ኢንጎሮን "የህግ እና/ወይም የእውነታ ስህተቶችን ሰርተው" እንደሆነ ወይም፣ ውሳኔ አሰጣጣቸውን እና/ወይም ስልጣናቸውን አለአግባብ ተጠቅመው እንደሆነ እንዲወስን የይግባኝ ሰሚውን ፍርድ ቤት እየጠየቁ መሆኑን ጽፈዋል።

ዳኛው ውሳኔውን የሰጡት ትረምፕ፣ ድርጅታቸውና ልጆቻቸውን ጨምሮ ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚዎቹ ከባንኮች እና ከሌሎችም ተቋማት የገንዘብ ብድር ለማግኘት ሲሉ፣ ሀብታቸውን እጅግ አጋንነው በማቅረብ ለዓመታት ማጭበርበር ፈጽመዋል በሚለው ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን በማረጋገጣቸው መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ከዳኛው የቅጣት ውሳኔዎች መካከል የትረምፕ ኩባንያዎችና ድርጅቶች በኒው ዮርክ ምንም ዐይነት የንግድ ሥራ እንዳይሠሩ ገደቦችን ያስቀምጣል፡፡

የዳኛ ኤንጎሮን ውሳኔ ከጸደቀ ትረምፕ ካላቸው ሐብት ብዛት ያለውን ይወስድባቸዋል፡፡ ዳኛው የወሰኑባቸው የ355 ሚሊዮን ዶላር መቀጮ እንዲከፍሉ ሲሆን ከወለድ ወደ 454 ሚሊዮን ገደማ ይደርሳል፡፡ ቅጣቱን ከፍለው እስኪጨርሱ በየቀኑ 112 ሺህ ዶላር ይጨመርባቸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG