በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችው ወረራ ሁለተኛ ዓመት ታሰበ


በኪቭ የመታሠቢያ ሥፍራ ላይ የአበባ ማስቀመጥ ሥነ ስርዓት (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 24, 2024)
በኪቭ የመታሠቢያ ሥፍራ ላይ የአበባ ማስቀመጥ ሥነ ስርዓት (ፎቶ ኤኤፍፒ የካቲት 24, 2024)

ሩሲያ በዩክሬን ላይ የፈፀመችው ወረራ ሁለተኛ ዓመት ትናንት ሲታሰብ፣ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አገራቸውን የደገፉትን ሁሉ አመስግነዋል።

“በዩክሬንም ሆነ በአካባቢው አገራት ያሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ እናት አገራቸው የፑቲን ጓሮ እንዳትሆን፣ እገዛው አስተዋጽኦ አድርጓል” ሲሉ ተናግረዋል ዜሌንስኪ።

ዜሌንስኪ ንግግራቸውን ያደረጉት ሩሲያ የትናንት ሁለት ዓመት ጥቃቷን በጀመረችበት ሆስቶሜል አየር ማረፊያ ሜዳ ላይ ቆመው ነው።

ዩክሬናውያን ቀኑን ሰማዕታቱን ለማክበር አበባ በማኖር፣ በለቅሶ እና ድል እንደሚያደርጉ ተስፋቸውን በመግለጽ አስበዋል። የሩሲያ ጥቃት የመቀዛቀዝ ምልክት ባላሳየበት በዚህ ወቅት፣ በዩክሬን ሕይወታቸውን የሚያጡት ሰዎች ቁጥር በመጨመር ላይ ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የጦርነቱን ሁለተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ የቡድን 7 ዓባል አገራት፣ አስፈላጊ ሆኖ እስከተገኘ ድረስ ለዩክሬን የሚሰጡትን ድጋፍ እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል።

ቡድኑ ባወጣው መግለጫ፤ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ለምታካሂደው ጦርነት ቻይና እና ኢራን ድጋፍ መስጠታቸውን አውግዘዋል።

ኢራን ለሩሲያ ሠራዊት የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆምም ጠይቀዋል። የቻይና ኩባንያዎች መሣሪያ እና ወታደራዊ ቁሶችን ለሞስኮ ማስተላለፋቸው እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG