በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካና እንግሊዝ የሁቲ ይዞታዎችን በጋራ ደበደቡ


በአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ጥር 22፣ 2024 የተለቀቀው ይህ ፎቶ ከእንግሊዝ እና ከሌሎችም አገራት ጋራ በመተባበር በሁቲ አማፂያን ላይ ድብደባ እንደተፈጸመ ያመለክታል (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥር 22፣ 2024)
በአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ ጥር 22፣ 2024 የተለቀቀው ይህ ፎቶ ከእንግሊዝ እና ከሌሎችም አገራት ጋራ በመተባበር በሁቲ አማፂያን ላይ ድብደባ እንደተፈጸመ ያመለክታል (ፎቶ ኤኤፍፒ ጥር 22፣ 2024)

የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ኃይሎች በየመን የሁቲ አማፂያን በርካታ ይዞታዎችን ትናንት ቅዳሜ መደብደባቸው ታውቋል።

የሁቲ አማጺያን በቅርቡ በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚጓጓዙ መርከቦች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት አጠናክረው መቀጠላቸው ይታወቃል።

የአሜሪካ እና የእንግሊዝ ተዋጊ ጄቶች 18 የሁቲ ይዞታዎችን መደብደባችውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የአሜሪካ ባለሥልጣን አስታውቀዋል። እነዚህ ይዞታዎችም፤ የሚሳዬል፣ የማስወንጨፊያዎች፣ የሮኬት፣ የድሮን እምንዲሁም የምድርና የውሃ ውስጥ መጓጓዣ ተሽከርካሪዎች ማከማቻዎች እንደነበሩ ታውቋል።

ካለፈው ወር የፈረንጆቹ ጥር 12 ወዲህ አሜሪካ እና እንግሊዝ በሁቲ አማፂያን ላይ በጋራ የተቀናጀ ጥቃት ሲያደርሱ ለአራተኛ ግዜ እንደሆነ ታውቋል።

አሜሪካ ግን በግሏ የሁቲ ዒላማዎችን በየቀኑ በመደብደብ ላይ መሆኗ ታውቋል። ተተኩሰው በአየር ላይ ያሉና በመርከቦች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሚምዘገዘጉ ሚሳዬሎችን እንዲሁም ድሮኖችንና ለመወንጨፍ የተዘጋጁ መሳሪያዎችን አሜሪካ ስትደበድብ ከርማለች፡፡

የአሜሪካ ጄቶች የሚነሱት በቀይ ባሕር ላይ ከሚገኘው ዩኤስ ኤስ ድዋይት አዘናወር አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ላይ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG