በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤኮዋስ በኒዤር ላይ ጥሎት የነበረውን ማዕቀብ አነሳ


በአቡጃ የተደረገው የኤኮዋስ ስብሰባ (ፎቶ ኤኤፍፒ፤ የካቲት 24፣2024)
በአቡጃ የተደረገው የኤኮዋስ ስብሰባ (ፎቶ ኤኤፍፒ፤ የካቲት 24፣2024)

የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) ትናንት በናይጄሪያ መዲና አቡጃ ላይ ባደረገው ስብሰባ፣ ባለፈው ዓመት የተፈጸመውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ፣ በኒዤር ላይ ጥሎት የነበረውን የጉዞ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ አንስቷል።

እርምጃው በኒዤርም ሆነ መፈንቅለ መንግስት በተካሄደባቸው የቀጠናው ሶስት ሌሎች አገራት ማለትም፣ ከቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ጊኒ ጋራ ንግግር እንዲደረግ እና ከቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመውጣት የደረሱበትን ውሳኔ እንዲቀለብሱ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

ከጉዳዩ ውስብስብነት አንፃር እንዲሁም በቀጠናው ዘላቂ ሠላም፣ ፀጥታ እና የፖለቲካ መረጋጋት ለማምጣት ገንቢ ውይይት ማድረጋቸው አስፈላጊ መሆኑን የናይጄሪያው ፕሬዝደንት ቦላ ቲኑቡ በስብሰባው ላይ ተናግረዋል።

የኤኮዋስ ኮሚሽን ፕሬዝደንት ኦማር ቱሬ በበኩላቸው፣ በኒዤር ላይ የተጣለው ማዕቀብ የተነሳው የአገሪቱን ሕዝብ ስቃይ ለመቀነሰ ሰብዓዊነትን መሠረት በማድረግ ነው ብለዋል።

የትናንት ቅዳሜ ስብሰባ የተደረገው፣ በአካባቢው ተደጋግሞ የሚታየው መፈንቅለ መንግስት የ49 ዓመቱን የቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ እንዳያፈርሰው በሚሰጋበት ወቅት ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG