በጋዛ የተኩስ አቁም ለማድረግ ያለመ ድርድር ከግብጽ፣ ቃጣር፣ አሜሪካ እና እስራኤል የተውጣጡ ባለሙያዎች እንዲሁም የሃማስ ተወካዮች ዶሃ ላይ መቀጠላቸውን አንድ ከመንግስት ጋር ግንኙነት ያለው የግብጽ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል።
በሞሳድ ኃላፊ ዴቪድ ባርኒያ የተመራ የእስራኤል ልዑክ ዓርብ ዕለት ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ገብቶ እንደነበር ታውቋል። ዓላማውም አዲስ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ እንዲሁም በሃማስ የተያዙ ታጋቾችን አስፈትቶ በምትኩ ፍልስጤማውያን እስረኞችን ለማስለቀቅ ውይይት ለማድረግ እንደሆነ ታውቃል።
የእስራኤል የጦር ካቢኔ በቃጣር ስብሰባ ላይ የሚሳተፍ ልዑክ ለመላክ ትናንት ቅዳሜ ስምምነት ላይ እንደደረሰ የስራኤል መገናኛ ዙሃን ዘግበዋል።
የቃጣሩ ስብሰባ የፓሪሱ ቀጣይ መሆኑን እና በማስከተልም በካይሮ እንደሚካሄድ ታውቋል።
ባለፈው ህዳር 100 ታጋቾችን በ240 የፍልስጤማውያን እስረኞች እንደተለዋወጡ ሁሉ፣ አሜሪካ ግብፅ እና ቃጣር ተመሳሳይ ልውውጥ እንዲደረግ በመጣር ላይ ናቸው።
በድርድሮቹ፣ ሐማስ እስራኤል ከጋዛ እንድትወጣና ተኩስ አስቁም እንዲደረግ ሲጠይቅ፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ምኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጥያቄውን “ቅዠት” ነው ሲሉ ገልጸውታል።
እስራኤል በደቡባዊቷ የጋዛ ከተማ ራፋ የምድር ጥቃት ለመፈጸም በማቀዷ የሰጉ 1.4 ሚሊዮን ፍልስጤማውያን ወደ ግብፅ ድንበር በመጠጋት በድንኳን ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ።
መድረክ / ፎረም