በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በጦርነቱ ሁለተኛ ዓመት በኦዴሳ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ሰው ሞተ


ዩክሬን ኪቭ
ዩክሬን ኪቭ

የዩክሬን ባለስልጣናት ሩሲያ በደቡባዊ የወደብ ከተማ ኦዴሳ አንድ የመኖሪያ ህንጻ ላይ በፈጸመችው ጥቃት አንድ ሰው ሲሞት ሌሎች ብዙዎች መጎዳታቸውን አስታወቁ።

ባለስልጣናቱ ትላንት አርብ ማምሻውን በተጸመው የሩሲያ ጥቃት ዩክሬን ብዙ የሩሲያ ድሮኖችን መታ መጣሏንም አስታውቀዋል። ይህ ጥቃት በዛሬው ዕለት የዩክሬን ወረራ ሁለተኛ ዓመት ለማክበር የተለያዩ የአውሮፓ መሪዎች በኪቭ ለመገኘት ወደ ዩክሬን እንደሚጓዙ እየታወቀ የተፈጸመ ነው፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን መሪ ኡርሱላ ቮንደር ሌን፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ፣ የቤልጄም ጠቅላይ ሚኒስትር አልክዛንደር ደኩሮ እና የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በባቡር ወደ ኪቭ ተጉዘዋል።

በተያያዘ ትላንት አርብ ማምሻውን የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት በሩሲያ ላይ 500 አዳዲስ ማዕቀቦችን መጣሉን አስታውቋል፡፡ ይህም የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ከጀመረ አንስቶ እጅግ ትልቁ ማዕቀብ መሆኑ ነው የተገለጸው። ማዕቀቡም የሩሲያ ተቃዋሚ አሌክሲ ናልቫኒ በእስር ላይ እንዳለ መሞቱን እና የዩክሬን ወረራን ሁለተኛ ዓመት በማስመልከት የተደረገ እርምጃ መሆኑን ዩናይትድ ስቴትስ አስታውቃለች።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG