በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመዱ ፍ/ቤት እስራኤል ከፍልስጥኤማውያን የይገባኛል ግዛቶች እንድትወጣ የሚጠይቅ ሐሳብ እንዳያቀርብ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ የህግ አማካሪ ሪቻርድ ቪሴክ በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ዘ ሄግ፣ ኔዘርላንድስ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ የህግ አማካሪ ሪቻርድ ቪሴክ በዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት ዘ ሄግ፣ ኔዘርላንድስ

ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት እስራኤል ከያዘቻቸው ፍልስጤማውያን ይገቡናል ከሚሏቸው ግዛቶች እንድትወጣ” የሚጠይቅ የሕግ አስተያየት እንዳያቀርብ ዩናይትድ ስቴትስ አሳሰበች።

ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ረቡዕ ባቀረበችው ተቃውሞ ፍርድ ቤቱ እስራኤል “ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ መውጣት አለባት” የሚል ሕግ አስተያየት መስጠት የለበትም ብላለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተጠባባቂ የህግ አማካሪ ሪቻርድ ቪሴክ 15 ዳኞች የተሰየሙበት ዓለም አቀፉ የፍትህ ፍርድ ቤት “በአንድ ወገን ድርጊት ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን ብቻ መሠረት ባደረጉ የህግ አስተያየቶች ለአሰርት ዓመታት የዘለቀውን የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት ለመፍታት መሞክር የለበትም” ብለዋል፡፡

በአንድ ወገን ድርጊት ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎችን  ብቻ መሠረት ባደረጉ የህግ አስተያየቶች ለአሰርት ዓመታት የዘለቀውን የእስራኤልና የፍልስጥኤም ግጭት ለመፍታት መሞክር የለበትም”

ፍርድ ቤቱ እስራኤል በያዘቻቸው ግዛቶች የምትከተላቸውን ፖሊሲዎች ህጋዊነት በሚመለከት አሳሪ ያልሆነ የውሳኔ አስተያየቱን እንዲሰጥ በመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበለትን ጥያቄ ከትናንት በስተያ ጀምሮ እየተመለከተ ነው፡፡

ቪሴክ ፍርድ ቤቱ የቀረበለትን ጥያቄ መመልከት የሚችለው "መሬት ለሰላም በሚለው መርህ እና ግዛቶችን በወረራ መያዝን በሚመለከተው ሕግ መርሕ ማዕቀፎች ውስጥ ነው “ብለዋል፡፡

ከቪሴክ ቀደም ብለው የኮሎምቢያ፡ የኩባ እና የግብጽ ተወካዮች የእስራኤልን ፖሊሲ ተቃውመዋል፡፡

የፍልስጤማውያንን ጨምሮ በድምሩ የ51 አገሮች ተወካዮች ለችሎቱ ንግግር እንደሚያደርጉ ተጠቁሟል፡፡

የፍልስጤም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሪያድ ማልኪ ፍርድ ቤቱ የፍልስጤም የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንዲያረጋግጥ እና የእስራኤል ወረራ ህገ-ወጥ መሆኑን እንዲያውጅ አሳስበዋል፡፡

እአአ በ1967 በተካሄደው ጦርነት እስራኤል ዌስት ባንክን ጋዛ ሰርጥን እና ምስራቅ እየሩሳሌምን መቆጣጠሯ ይታወሳል፡፡ ፍልሥጥኤማውያን እስራኤል ሦስቱንም ግዛቶች እንድትለቅቅ የሚጠይቁ ሲሆን እስራኤል በበኩሏ የዌስት ባንክ ጉዳይ አከራካሪ በመሆኑ መጻዒ ዕጣው በድርድር መወሰን አለበት ብላለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG