በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ሩዋንዳ ለኤም 23 አማፂያን ትሰጣለች ያለችውን ድጋፍ አወገዘች


በኢትዮጵያ መዲና፣ አዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ፣ ተሳታፊዎች በምስራቅ ኮንጎ የሚካሄደውን ግጭት የሚቃወም ድምፅ አሰምተዋል - የካቲት 17፣ 2024
በኢትዮጵያ መዲና፣ አዲስ አበባ እየተካሄደ ባለው 37ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ፣ ተሳታፊዎች በምስራቅ ኮንጎ የሚካሄደውን ግጭት የሚቃወም ድምፅ አሰምተዋል - የካቲት 17፣ 2024

ዩናይትድ ስቴትስ ሩዋንዳ በምስራቅ ኮንጎ ለሚንቀሳቀሱት እና በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ለሆኑት የኤም 23 ታጣቂ ቡድኖች ትሰጣለች ያለችው ድጋፍ አወገዘች። ታጣቂ ቡድኑ ከማንኛውም ጥቃት እንዲታቀብም ጥሪ አቅርባለች።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ "በሩዋንዳ በሚደገፉ እና በአሜሪካ እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ማዕቀብ በተጣለባቸው ኤም 23 ታጣቂ ቡድኖች የተባባሰውን ሁከትን እና ብጥብጥ" አጥብቆ ተችቷል። ሩዋንዳም፣ ሁሉንም የመከላከያ ኃይል አባላቷን በአስቸኳይ ከኮንጎ እንድታስወጣ እና የንፁሃን ዜጎችን እና ሰላም አስከባሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ የጣለውን፣ ከምድር ወደ አየር የሚወነጨፍ የሚሳይል ሥርዓቷን እንድትስወግድ ጠይቋል።

በተጨማሪም፣ አማፂያኑ አሁን ካሉበት በሰሜን ኪቩ ግዛት ውስጥ የሚገኙ ሁለት ከተሞች እንዲያፈገፍጉም አሳስቧል።

አሜሪካ ያወጣችው መግለጫ፣ መንግስቷ ከኤም 23 ቡድን ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው በተደጋጋሚ በምትገልፀው ሩዋንዳ ላይ ጫና ሊፈጥር ይችላል።

የኮንጎ ፕሬዝዳንት ፌሊክስ ሺሴኬዲ፣ ሩዋንዳ ታጣቂዎቹን በመደጋፍ ኮንጎን ታተራምሳለች በማለት ይከሳሉ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለሙያዎች ቀደም ሲል ባወጡት ሪፖርት፣ የሩዋንዳ የጦር ኃይል አባላት M23 ቡድንን ለመደገፍ ዘመቻ ሲያደርጉ እንደነበር የሚያሳይ “ጠንካራ ማስረጃ” እንዳላቸው አስታወቀው ነበር።።

የሰሜን ኪቩ ግዛት ዋና ከተማ እና በክልሉ ትልቁ ከተማ በሆነችው ጎማ አቅራቢያ ውጊያው ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ፣ አማፅያኑ ከተማዋን በቅርቡ እንደሚቆጣጠሩ እያስፈራሩ ነው።

የህዳር ወር ወዲህ ትጥቅ ትግሉ በምስራቅ ኮንጎ የሚኖሩ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቅሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG