በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሴኔጋል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እጩ ተፎካካሪ ከእስር እንዲለቀቁ ጥሪ ቀረበ


ፋይል - የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ቡድኖች የምርጫው ቀን እንዲከበር የሚጠይቅ ሰልፍ በዳካር ባካሄዱበት ወቅት
ፋይል - የሲቪል ማህበራት እና የፖለቲካ ቡድኖች የምርጫው ቀን እንዲከበር የሚጠይቅ ሰልፍ በዳካር ባካሄዱበት ወቅት

በሴኔጋል በሚካሄደው ፕሬዛንታዊ ምርጫ እጩ ተፎካካሪ የሆኑት ተቃዋሚ ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ ደጋፊዎች፣ ሕገመንግሥቱ በሚያዘው "እኩል አያያዝ" መሠረት በአስቸኳይ ከእስር እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

የዲዮማዬ ፕሬዝድናታዊ ጥምረት ባወጣው መግለጫ "ሁሉም እጩዎች በእኩልነት የመስተናገድ ሕገ መንግሥታዊ መርሆዎች ተጠቃሚ መሆን አለባቸው" ብሏል።

ጥምረቱ አክሎ፣ በእስር ላይ የሚገኙት የተቃዋሚው ፓስቴፍ ፓርቲ መሪ ኦስማን ሶንኮም በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል።

የሕገ መንግሥቱ ፍርድ ቤት የሶንኮን ዕጩነት ውድቅ ያደረገ ሲሆን፣ ፋዬ እና ሌሎች 20 ሰዎች ግን በእጩነት መቅረባቸውን ተቀብሏል።

ሶንኮ በቀረባቸው አመፅ የማነሳሳት፣ በሽብርተኝነት ከሚጠረጠሩ ወንጀለኞች ጋር ግንኙነት የመፍጠር እና መንግስትን የመጉዳት ክስ፣ እ.አ.አ ከሐምሌ 2023 ጀምሮ በእስር ላይ ናቸው።

የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ወር ባወጣው መግለጫ፣ ሕገ መንግስታዊ ምክርቤቱ ያፀደቃቸው እጩዎች በእኩልነት የምርጫ ቅስቀሳ እንዲያካሂዱ ሊፈቀድላቸው ይገባል ብሏል።

በሴኔጋል የፖለቲካ እስረኛ የለም የሚሉት ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል በበኩላቸው፣ በቅርቡ እስር ላይ የነበሩ በርካታ የተቃዋሚ ደጋፊዎች በነፃ እንዲለቀቁ አድርገዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG